በአዲሱ የውድድር ዘመን ማለትም በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም የመጫወቻ ሜዳ ችግር ትልቁ ፈተና እንደሚሆን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ተናግረዋል።
በተጠናቀቀው የውድድር አመት ምንም እንኳን ከቀደሙት የውድድር ጊዜያቶች የተሻለ ነዉ ቢባልም ነገር ግን በተለመደዉ የመጫወቻ ሜዳ ምቹ አለመሆን ምክንያት ፕሪሚየር ሊጉ በተደጋጋሚ ሲቆራረጥ እና ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜያት ሲተላለፉ የነበረ ሲሆን ፤ በቀጣዩ የውድድር ዘመንም ይሄዉ ጉዳይ እንቅፋት እንደሚሆን እና የሊጉ ጥራት ላይም ተፅዕኖ እንደሚኖረው የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሜቴ ሰብሳቢው ተናግረዋል።
እንደሚታወቀው ከቀናት በፊት በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት ላይ ደግሞ የአክሲዮን ማህበሩ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ችግሩ መኖሩን ገልፀዉ ፤ በቀጣዩ አመት ከገና በዓል በኋላ ግን ማለትም ታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ፕሪሚየር ሊጉ ወደ አዲስአበባ እንደሚመለስ መናገራቸው ይታወሳል።