የቀድሞ አሰልጣኙን ዉበቱ አባተ በዋና አሰልጣኝነት የሾመዉ ፋሲል ከነማ በቅርቡ በአሜሪካዉ ክለብ የሙከራ ጊዜ ማሳለፍ የቻለዉን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ማስፈረሙ ታውቋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ለኢትዮጵያ ቡና ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት የቻለዉ እንዲሁም ከሀገር ውጭ ደግሞ ለሩሲያዉ ክለብ አንዚማካቻካላ እና ለሁለት የግብፅ ክለቦች መጫወት የቻለዉ ጋቶች ፓኖም በአንድ አመት የኮንትራት ውል ፋሲል ከነማን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።