የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ለ15ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃግብር በዳኝነት የተመደቡትን 16 ዳኞች ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት በመሃል ዳኝነት የተመረጡት 10 ዳኞች ኢንተ.አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ፣ ኢንተ.አርቢትር በላይ ታደሰ፣ ኢንተ.አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ፣ ኢንተ.አሸብር ሰቦቃ ፣ ፌዴራል አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ፣ ፌዴራል አርቢትር አዳነ ወርቁ፣ ፌዴራል አርቢትር ዳንኤል ይታገሱ፣ ፌዴራል አርቢትር ሰለሞን አሸብርና ና መሆናቸው ታውቋል።
በረዳት ዳኝነት የተመረጡት ሁለቱ ወንድማማቾች ፌዴራል ረዳት ዳኞች መሃመድ ሁሴንና ሚፍታህ ሁሴንን ጨምሮ ደግሞ ፌዴ. ረዳት አርቢትር ዳንኤል ጥበቡ፣ ፌዴ. ረዳት አርቢትር አስቻለሁ ወርቁ፣ ፌዴ. ረዳት አርቢትር ሶርሳ ዱጉማ፣ ፌዴራል .ረዳት አርቢትር ማህደር ማረኝ፣ ፌዴራል ረዳት አርቢትር እሱባለሁ መብራቱና ፌዴ. ረዳት አርቢትር ታምሩ አደም መሆናቸው ታውቋል።
16ቱ አርቢትሮች ዛሬ ተጠቃለው ድሬዳዋ የገቡ ሲሆን አወዳዳሪ አካሉ ከዳኞች ኮሚቴ ከተወከለው ባለሙያ ጋር በመሆን ከ16ቱ ዳኞች ጨዋታዎችን የሚመሩትን አርቢትሮች ይመድባሉ ተብሎም ይጠበቃል
- ማሰታውቂያ -
ሊግ ኩባንያው ባወጣው መርሃግብር መሠረት ውድድሩ ነገ የሚቀጥል ሲሆን ከቀኑ 10 እና ከምሽቱ 1 ሰዓት ጨዋታዎቹ በድሬዳዋ የሚካሄዱ መሆናቸው ታውቋል። ሃሙስ አርባምንጭ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ዓርብ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ መድን ለገጣፎ ለገዳዲ ከመቻል ቅዳሜ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከተማ እሁድ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ ባህርዳር ከተማ ከወላይታ ድቻ ይጫወታሉ።
ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብና 22 ግብ ሲመራ ኢትዮጵያ መድንና ባህር ዳር ከተማ በ27 እና 26 ነጥቦች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የፈረሰኞቹ እስማኤል ኦሮ አጎሮ በ14 ግብ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን እየመራ ይገኛል።