መነሻ ገጽ ለገጣፎ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ ከዛሬው ጨዋታ ራሱን ሊያገል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
ለገጣፎ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ለገጣፎ ለገዳዲ ከዛሬው ጨዋታ ራሱን ሊያገል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

አጋራ
አጋራ

*…ፌዴሬሽኑ ህጋዊ ነው ያላቸውን ተጨዋቾች ዝርዝር
ለሊግ ኩባንያው ልኳል…..

ለገጣፎ ለገዳዲ በሊግ ኩባንያ የተወሰደው ተገቢነት የሌለው ርምጃ ካልተስተካከለ ከዛሬው የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ራሳችንን እናገላለን” ሲል ክለቡ አስታወቀ።

በሊጉ የ14ኛ ሳምንት መርሃግብር ያስፈረማቸውን ተጨዋቾች ከሁለተኛው ዙር በኋላ እንጂ መሠለፍ አይችሉም በሚል በመከልከላቸው በ12 ተጨዋች ብቻ የገቡት ለገጣፎዎች በሲዳማ ቡና 2ለ0 የተሸነፉ ሲሆን ከወራጅ ቀጠና እንዲያወጣቸው በቀጠሩት አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ ላይ ሌላ ጫና ፈጥሯል።

ሊግ ኮሚቴው የሲዳማ ቡናና የለገጣፍ ለገዳዲ ጨዋታ አስቀድሞ በተነሳው ውዝግብ ዙሪያ አሰልጣኙና ቡድን መሪውን ትላንት ጠዋት ጠርተው ያነጋገሩ ሲሆን ውዝግብ ከሚያስነሱና ልዩነት ከሚፈጥሩ አስተያየቶች እንዲቆጠቡ የሚዲያ ፍጆታ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል።

ሊግ ከባንያው አንደኛ ዙር ሳያልቅ የዝውውር መስኮቱን መክፈቱ የፈጠረውን ክፍተት ከማረም ባለበት ውሳኔው መቀጠሉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው የገለጹት የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ እንዳለ.. ” ፌዴሬሽኑ መብታችንን እንዲያስከብር ጠይቀናል በሊግ ኩባንያው አካሄድና ውሳኔ ተከፍተናል ውሳኔውን ገምግሞ ማስተካከያ የማያደርግና ያስፈረምናቸውን ተጨዋቾች እንድንጠቀም የማይፈቄድ ከሆነ ከዛሬው የመቻል ጨዋታ ራሳችንን አግልለናል ይህንንም ለሊግ ኩባንያው አሳውቀናል በደሉና ተገቢ ያልሆነው አካሄድ በኛ መቆም አለበት” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ሊግ ኩባንያው በተዘጋው የዝውውር መስኮት የፈረሙ ተጨዋችችን መጠቀም የሚቻለው ከ16ኛው ሳምንት ጀምሮ ነው በ14ኛ እና በ15ኛ ሳምንት የተጠቀመ ካለ በፎርፌ ይቀጣል” የሚለውን ደብዳቤ ለ16ቱም ክለቦች የጻፈው ለገጣፎዎች ጥያቄ ካነሱና የሊግ ኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ከለገጣፎ ስራ አስኪያጅ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ የክለቡን ቅሬታ አጠናክሮታል።

ዛሬ ጠዋት ከክለቡ ምንጭ በተገኘ መረጃ ፌዴሬሽኑ ህጋዊ የሚላቸውና ዛሬም መጫወት የሚችሉ ተጨዋቾችን ዝርዝር ለሊግ ኩባንያና ለክለቡ መላኩ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...