▶️ ከውል ነጻ በመሆኑ የፊፋ ህግ ይደግፈዋል
ተብሏል…
ባህርዳር ከተማ ያስገባውን ይግባኝ ውድቅ ያደረገው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኦሴ ማውሊን የፋሲል ከነማ ዝውውር አጸደቀ።
ተጨዋቹ ከባህርዳር ከተማ ጋር ያለው ውል መቋረጡን ተከትሎ ክስ የመሰረተ ሲሆን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በውል ዘመኑ ላይ ያለው ደመወዝ ይከፈለው ወደፈለገበትም ክለብ መዘዋወር ይችላል ብሎ የሰጠውን ውሳኔ ባህርዳሮች ይግባኝ ቢሉም ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውድቅ አድርጎታል ።
በህጉ መሠረት ይግባኝ ጠያቂ አካል ውሳኔ በደረሰው በሰባት ቀን ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ እንዳለበት ነገር ግን በሶስት ቀን ውስጥ እንደሚከሱና ይግባኝ እንደሚሉ አስቀድመው ማሳወቅ አለባቸው ይላል ባህርዳሮች በይግባኝ የመጠየቂያ ቀነ ገደብ መሠረት በሰባት ቀን ውስጥ ይጎባኝ ቢሉም ቀድመው እንደሚከሱ መግለጽ ባለባቸው የቀን ገደብ ውስጥ ባለማሳወቃቸው ይግባኙ ውድቅ ሆኖ ያስያዙት ገንዘብ ገቢ እንዲሆን ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
ጋናዊው አጥቂ ኦሴ ማውሊ ከውል ውጪ በመሆኑ ፊፋ ከውል ውጪ የሆነ ተጨዋች የዝውውር መስኮቱ ቢዘጋም ወደፈለገበት ክለብ መግባት ይችላል በሚለው ደንቡ መሰረት ወደ ፋሲል ከነማ እንዲገባ ተፈቅዶለታል።ይህም ከነ ሙጂብ ቃሲምና ኦኪኪ አፎላቢ በኋላ የሳሳውን የአሰልጣኘ አሸናፊ በቀለ የፊት መስመርን አስፈሪ አድርጎታል። አሰልጣኙ በነገው ጠንካራ ጨዋታ ላይ ያሰልፈው አያሰልፈው የወጣ መረጃ ባይኖርም ከግጥሚያው ጥንካሬ አንጻር ሊያሰልፈው እንደሚችል ይገመታል።
አጥቂው ኦሴ ማውሊ ከሀገር ውጪም ቢሆን ከውል ነጻ በመሆኑ ወደፈለገበት ክለብ የመግባት ዕድል ያለው ቢሆንም ፌዴሬሽኑ የሀገር ውስጡን ዝውውር ማድረግን እንደፈቀደለት የደረሰን መረጃ ያስረዳል። ተጨዋቹ መቀለ 70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ፣ ሰበታ ከተማና
ባህርዳር ከተማ ከተጫወተ በኋላ ዛሬ ደግሞ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሶ ለቀጣዮቹ 12 ወራት ለአጼዎች ዳግም ግልጋሎት ለመስጠት ተስማምቷል።