➡️ ጉዳዩ መንግስት ጋር ደርሷል…
➡️ የፌዴሬሽኑ ምላሽ እየተጠበቀ ነው…
➡️ መቻሎች ፎርፌ አግኝተዋል..
ለገጣፎ ለገዳዲ “በሊግ ካምፓኒው ዕገወጥ ድርጊትና የመብት ጥሰት እየተፈጸመብኝ ነው” ሲል ከሰሰ
ክለቡ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ “በሊግ ኩባንያው ተደጋጋሚ በደል ሲደርስብን እንደነበረና ፌዴሬሽኑ ህጋዊ ናቸው ያላቸውን ተጨዋቾች አልቀበልም በማለት በህገወጥ መንገድ የፌዴሬሽኑን ህግ ወደጎን በመተው የራሱን አቋም እያራመደ ቆይቷል” ሲል ከሷል።
ፌዴሬሽን ህጋዊ ናቸው ያላቸውን ተጨዋቾች ዝርዝር ለኛም ሆነ ለሊግ ኩባንያው ልኳል ያለው የክለቡ ደብዳቤ ሊግ ኩባንያው ህገወጥ ተግባሩን ማቆም አልቻለም ያም ሆኖ እኛ በተላከልን ህጋዊ ተጨዋቾች ዝርዝር መሠረት ወደ ጨዋታ ስናስገባ አወዳዳሪው አይቻልም ቢል በክለቡም ሆነ በክለቡ አባላት ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ችግር አወዳዳሪው አካል እንዲጠየቅልን እንፈልጋለን” ሲል ለፌዴሬሽኑ በጻፈውና በግልባጭ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ለሚመለከታየው አካላት ባደረሰው ደብዳቤ ጠይቋል።
- ማሰታውቂያ -
ምሽት ላይ ከድሬዳዋ በተሰማ ዜና ክለቡ ህጋዊ ናቸው ያላቸውን ተጨዋቾቹን ይዞ ወደ ሜዳ ሊገባ ሲል በአወዳዳሪ አካል የተከለከለ ሲሆን ለዲ ኤስ ቲቪ የደረሰው የሊግ ካምፓኒው ዝርዝር ህጋዊ ናቸው ያላቸው አራት ተጨዋቾች ብቻ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል
የፌዴሬሽኑን የህጋዊነት ማረጋገጫ ቲሴራ ያገኙትን ተጨዋቾች ህጋዊ አይደሉም ብሎ ሊግ ካምፓኒው ሲከለክል የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከመነጋገር ውጪ መብታቸውን ከማስከበር አንጻር ተገቢ ነው ያሉትን ርምጃ አለመውሰዳቸው እያነጋገረ ነው።
በሊግ ኩባንያውና በለገጣፎ ለገዳዲ አለመግባባት ዛሬ የነበረው ጨዋታ ያልተካሄደ ሲሆን መቻሎች 30 ደቂቃውን ጠብቀው ፎርፌ አግኝተው ከሜዳው ወጥተዋል።