ድሬዳዋ ከነማ

ድሬዳዋ ከነማ 

አሰልጣኝ   ዘላለም ሽፈራው

dire-dawa-city-fc

ምስረታ 1996

ድሬደዋ ከነማ በ 1996 ተመስርቶ በ 1998 ብሔራዊ ሊግ መግባት ቻለ፡፡  በ 2000 ደግሞ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቀለ፡፡ ለሦስት አመት በሊጉ ሲቆይ ላመውረድ በመታገል ነው፡፡ ይሁንና በመጨረሻው እየተሳካለት በሊጉ ታይቷል፡፡

ምስረታ

ድሬደዋ ከነማ ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበራትን የድሬደዋ ከተማን እንዲወክል የተቋቋመው በ 1996 ዓ/ም ነበር፡፡ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ጭምር የሆኑ ክለቦች ባለቤት የነበረችው ድሬደዋ እግር ኳስ ተዳክሟል በሚል ወደ ቀድሞ ስፍራን መመለስ አላማ በደረ…..ነው የተቋቋመው ገናና ስም ለመመለስ የተቋቋመው ድሬደዋ ከነማ በ 1997 ለተደረገ የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ውድድርና ግምገማ የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ ወደ ብሔራዊ ሊግ እንዲያልፍ ተወሰነ፡፡ እናም በ 1998 በብሔራዊ ሊግ ለመወዳደር በቃ፡፡


በብሔራዊ ሊግ

ድሬደዋ ከነማ በተሳተፍበት የመጀመሪያ አመት ውጤታማ አልሆነም በቀጣዩ አመት 1999 ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበትን ውድድር በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ሻምፒዮን በመሆን ጭምር ነው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያለፈው፡፡ በተለይ ከሰበታ ከነማና ደደቢት ጋር የተደረገው ፉክክር ጠንካራ ነበር፡፡

በፕሪሚየር ሊግ

 

በ 1999 ብሄራዊ ሊግ ስኬታማ የሆነው ድሬደዋ ከነማ በአዲሱ ሚሊኒየም 2000 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ ቻለ፡፡ ይሁንና ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን አልቻለም፡፡ በ 2001 ዓ/ምም ቢሆን ላለመውረድ መታገል ነበር ቀዳሚ ስራው፡፡ በተለይ የመጀመሪያው ዙር የሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ የመጨረሻ ጠርዝ ይዞ ማጠናቀቁ በቀጣይ አመት ወደ መጣበት ብሔራዊ ሊግ መመለሱ አይቀርም የሚል ግምት አሰጥቶት ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ የመጀመሪያዎቹን አራት ጨዋታዎች በተከታታይ በማሸነፍ አንሰራራ፡፡ የቀጣይ ጨዋታዎችም ጥሩ ነጥብ በመሰብሰቡ ከመውረድ ተርፏል፡፡

          በ 2002 መጀመሪያ በሊጉ እንዲቆይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተለትን አሸናፊን ግርማን በሜታ አቦ ቢራ ተነጠቀ፡፡ በሊጉም ስኬታማ አልሆነም ይሁንና እንዳለፈው አመት ሁሉ በሁለተኛው አጋማሽ አንሰራራ፡፡ በሜዳው ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ካሸነፈ በኃላ ወደ ሀዋሳ በማቅናት ከደቡብ ፖሊስ አቻ ተለያይቷል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ባንኮችን ካሸነፈ በኃላ ድሬደዋ ላይ መድንን መድገሙ ነጥቡን ከፍ አደረገለት፡፡