መከላከያ ስፖርት ክለብ

መከላከያ 

መከላከያ ስፖርት ክለብ                                                    defence fc

ዋና አሰልጣኝ – ሻለቃ በለጠ ገብረኪዳን 

/አሰልጣኝ  ምንያምር ጸጋዬ

የህክምና ባለሙያ ፡- ቾንቤ ቦካን 

የበረኛ አሰልጣኝ :- ተረፈ ጉደታ

የቡድን መሪ  ሻበል ሙሉ ባራኪ 

 መከላከያ ስፖርት ክለብ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሚንቀሳቀስ የስፖርት ክለብ ሲሆን ከአፄ ሀይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ መንግስታት እየተወዳደረ ይገኛል፡፡ ጦር ሰራዊት፣ መቻልና መከላከያ የሚሉ ስያሜዎችን አፈራርቋል፡፡ ቀደም ባሉት ዘመን በኢትዮጵያ ሻምፒዮን እና በጥሎ ሻምፒዮና በተደጋጋሚ ሻምፒዮን መሆን ችሏል፡፡ በአዲስ መልክ ከተዋቀረም በኃላም በ1998 የጥሎ ማለፍ ዋንጫን አግኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡

ምስረታ 

የመከላከያ ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1937 ዓ/ም ከጣልያን ወረራ በኃላ አፄ ሀይለ ስላሴ ወደ መንበራቸው ሲመለሱ በጦር ሰራዊቱ ስር ነበር ስያሜውም የጦር ሰራዊት ስፖርት ክለብ የሚል ነበር፡፡ ክለቡ በተመሰረተበት አመት የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ባልታወቀ ሁኔታ ቢቋረጥም በጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና በ 1938 የጥሎ ማለፉን ዋንጫ አነሳ፡፡ በ 1939 እና የኢትዮጵያ ሻምፒዮና በድጋሚ በተጀመረበት 1940 ውጤት አልቀናውም፡፡ በ 1941 ግን ሁለቱንም ዋንጫወችን በማንሳት ውጤታማ ሆነ፡፡ የጥሎ ማለፉን በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም ለማሸነፍ ሀትሪክ ሰራ፡፡ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ዓ/ም ከ 1943 የበላይነት ተቆጣጠረ፡፡ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ከ 1946 ጀመሮ ስያሜውን ወደ መቻል ስፖርት ክለብ የቀየረው ክለቡ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን መሆን የቻለው በ 1948 ነበር፡፡ ከዚህ በኃላ ወደ ውጤት የተመለሰው ከ 20 አመት በኃላ በ 1967 የጥሎ ማለፉ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ የክለቡ በመቻል በሆነበት ወቅት ነበር በቀጣይነትም በ 1968፣ 1974፣ 1976፣ 1988 እና 1981 የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ የክለቡ በመቻል ስም እየተጠራ የመጨረሻ ዋንጫው የሆነውም በ 1982 ዓ/ም ያነሳው የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ነው፡፡ ከ 1983 ዓ/ም በኃላ ኢህዴግ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኃላ የመከላከያ ስፖርት ክለብ በድጋሚ ለመመስረት ሥስት አመታቱን ወስዷል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የተቀላቀለው በ 1998 ሲሆን እስካሁንም ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡