ደደቢት

ደደቢት 

ስም ፡ ደደቢት ስፖርት ክለብ – ምስረታ 1989 ዓ/ም

                                                      17262

ዋና አሰልጣኝ  ኤሌያስ ኢብራሂም

/አሰልጣኝ – ደብሮም ሐጎስ

የበረኛ አሰልጣኝ :- ጸጋጸአብ አስገዶም

የህክምና ባለሙያ ጥበበ አለመ 

 

አምበል 

የቡድን መሪ – 

ደደቢት ስፖርት ክለብ በክለቡ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም መስራችነት የተቋቋመ የእግር ኳስ ክለብ ነው፡፡ በ1989 ከ9 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በመመልመል በጀመረው ስልጠና የተመሰረተው ክለቡ አዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዬን፣ የክልል ክለቦች ሻምፒዮናና ብሔራዊ ሊግን በማለፉ የሀገሪቱ ቁጥር አንድ ውድድር ፕሪሚየር ሊግ ላይ ደርሷል፡፡

ምስረታ

ደደቢት የስፖርት ክለብ እንዲመሰረት ከሀሳብ አምጭነት ጀምሮ እውን እንዲሆን ያስቻሉት የክለቡ ፕሬዚዳት ኮ/ል አወል አብዱራሂም ናቸው፡፡ ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል ባደረገው ትግል የተሳተፉት ኮ/ል አወል ኢህአዴግ ሀገሪቷን ከቆጣጠረ ከ1983 ዓ/ም በኃላ አዲስ አበባ ስታዲየም ይገቡና እግር ኳስ ይመለከቱ ነበር፡፡ በሂደትም የመብራት ኃይል ደጋፊ ይሆናሉ፡፡ ድጋፋቸው የልምምድ ሜዳ ድረስ በመሄድ ማበረታቻ እስከ መስጠት የዘለቀ ነበር፡፡ ይሁንና በሂደት ባጠቃላይ የሀገሪቱ ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት ሲያሳይ መመልከት አልቻሉም፡፡ እናም እኔስ የበኩሌን አስተዋፅኦ ለምን አላበረክትም በሚል ስሜት ከታዳጊዎች ፕሮጀክት የሚጀምር ክለብ ለመመስረት ይነሳሉ፡፡ ለጓደኖቻቸው ሳያማክሩ በ1980 እምብዛም ተቀባይነት  አላገኙም፡፡ ከአመት በኃላ በ1989 በድጋሚ ሀሳቡን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ አድሜያቸው ከዘጠኝ አመት በታች የሆኑ 25 ህፃናትን በመመልመል እውን ሆነ ደደቢት እግር ኳስ ክለብ እውን ሆነ፡፡ ደደቢት የሕወሐት የትጥቅ ትግል መነሻ ስፍራ ሲሆን ኮ/ል አወል ይህን በማሰብ ክለቡን በዚህ ስፍራ ሠይመውታል፡፡

እስከ ብሔራዊ ሊግ 

በ1990 ጥቅምት 21 ቀን ላይ የክለቡ ታዳጊ ህፃናትን የመጀመሪያው መደበኛ ጨዋታ አደረጉ፡፡ መታሰቢያነቱ በመቀሌው የሀይደር ት/ቤት የአየር ቦምብ ድብደባ ለተጎዱ ህፃናት ያደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ከወረዳ 21 ቀበሌ 09 የታዳጊዎች ቡድን ጋር አደረጉ፡፡ ደደቢት የ2ለ0 ድል ባለቤት ሲሆን ከ6000 ብር በላይ ገቢ በማሰባሰብ ጥቃት ለደረሰባቸው ህፃናት እርዳታ ተላከ በ1992 በአዲስ አበባ ከ13 ዓመት በታች ፕሮጀክቶች መካከል የተደረገውን ውድድር በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ በቀጣዬቹ ሁለት  አመታትም ተመሳሳይ ውጤት አስመዘገበ፡፡ በ1996 ከ17 አመት በታች በመሳተፍ ዋንጫ በማንሳት ውጤታማ ሆነ፡፡ በ1998 በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀባይነት በማግኘቱ የአዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዬን ላይ መሳተፍ ቻለ፡፡ በመጀመሪያው አመትም ወደ ከፍተኛ ዲቪዚዬን የሚያሳልፈውን ነጥብ በማግኘቱ በ1999 ከፍተኛ ዲቪዚዬን ተቀላቀለ፡፡ በከፍተኛ ዲቪዚዬን ሻምፒዬን በመሆን ዋንጫ ከማንሳትም ባሻገር ሀዋሳ ላይ ወደ ተካሔደው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዬና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በመወከል የሚተፉበት እድል አገኘ፡፡ ሀዋሳ ላይም በፍፃሜው ጨዋታ ሰበታ ከነማን በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ እኛም ከአመርቂ ውጤት ጋር ብሔራዊ ሊግ ተቀላቀለ፡፡

ብሔራዊ ሊግና ውጣ ውረዱ  

የደደቢት የመጀመሪያው አመት የብሔራዊ ሊግ ቆይታ 2000 በከባድ ፉክክር የተካሄደ ነበር፡፡ በተለይ ደደቢት ከድሬደዋ ከነማና ሰበታ ከነማ ጋር ያደረገው ትንቅንቅ እስከመጨረሻ ጨዋታ ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡ ከሦስቱ ክለቦች ሁለቱ ወደ ፕሪሚየርሊጉ ያልፋሉ፡፡ በመጨረሻው ጨዋታ ድሬደዋ ተጋጣሚውን በቀላሉ አሸንፎ ሲያልፍ እርስ በእርስ የተገናኙት ደደቢትና ሰበታ ጨዋታ የበለጠ ተጠባቂ ሆነ፡፡ ሁለቱም እኩል ነጥብ ነበራቸው ይሁንና የተሻለ ግብ ክፍያ የነበረው ሰበታ አቻ መውጣት ይበቃው ነበር እናም ጨዋታው በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ደደቢት አመቱን በአሳዛኝ ሁኔታ አጠናቀቀ፡፡

በሁለተኛው አመት የሊጉ ቆይታው 2001 በሁለት ምድብ የተከፈለውን ውድድር ምድብ “ለ” በሠፊ ልዩነት በመምራት አጠናቀቀ ቀደም ሲል ከየምድባቸው አንደኛ የሆኑ ቡድኖች ያልፋሉ የተባለ ቢሆንም ኃላ ላይ ከየምድቡ ሁለት ቡድኖች የአንድ ዙር ውድድር ካደረጉ በኃላ የተሻሉት ሁለቱ እንዲያልፉ ተወሰነ፡፡ ደብረዘይት፣ ሜታቢራ፣ ሲዳማ ቡና፣ ከነማ፣ የአንድ ዙር ወድድር አደረጉ፡፡ ደደቢት በመጀመሪያ በሜታ ቀጥሎም በሲዳማ ቡና በመሸነፉ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ተዘጋ፡፡ ከዚህ በኃላ ክለቡ የተገቢነት ጥያቄ በማንሳት ከፌዴሬሽኑ ጋር ክርክር ገጠመ፡፡ ክለቦቹም የተስማሙበትና የተቀበሉት የመጀመሪያው የወድድር ደንብ መቀየሩ አግባብነት የለውም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማለፍ አለብን በማለት ተከራከረ፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ ስራ አስፈፃሚ ሲተካ ችግሩን ለመቅረፍ ይዘይዳል፡፡ ዘዴው ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱት ትራንስ ኢትዮጵያና ኒያላ ከብሔራዊ ሊጉ ማለፍ ካልቻሉት  ደደቢትና ሻሸመኔ ከነማ ጋር የአንድ ዙር ውድድር እንዲያደርጉና የተሻሉት ሁለቱ እንዲያልፉ ይወሰናል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ቁጥርም ወደ 18 ያድጋል፡፡ ሻሸመኔ ራሱን ሲያገል ደደቢትና ትራንስ ኒያላን አሸንፈው ሊጉን ተቀላቀሉ፡፡ እናም ደደቢት ለዘመናት ሲያልመው የነበረው ፕሪሚየር ሊጉን የመቀላቀል አላማ በተመሰረተ በ12 አመቱ አሳካ፡፡

በፕሪሚየር ሊግ

ደደቢት በ2002 ፕሪሚየር ሊጉን ሲቀላቀል በርካታ ተጫዋቾች ለከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በማስመጣት ነበር፡፡ ሙሉጌታ ምህረት ዳንኤል ደርቤ፣ ፍፁም ተፈሪ፣ ጀማል ጣሰው ከሀዋሳ ከነማ፣ ጌታነህ ከበደ ከደቡብ ፖሊስ፣ታጋይ አማረ ከመትሀራ እና ኤፍሬም ዘሩን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ መጥቷል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተንም ከአዳማ በማስመጣት ክለቡን ለማጠናከር ጥረት ተደርጓል፡፡ ደደቢት ወደ ውድድሩ ሲገባ ከተጠበቀው በላይ ውጤታማ ሆነ፡፡ በመጀመሪያው ዙር ካደረጋቸው 17 ጨዋታዎች ወደ አምቦ በማቅናት በሙገር ሲሚንቶ ከመሸነፉ በቀር በ16 ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡ የመጀመሪያ ዙር ሲያጠናቅቅም ተከታዩን ቅ/ጊዬርጊስን በሰባት ነጥብ በመብለጥ ነበር፡፡

ሁለተኛው ዙር ሲጀመር ደደቢት ከፌደሬሽኑ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ፡፡ ኢንተርናሽናል ጨዋታ የነበረበት ቅ/ጊዮርጊስ ሆን ተብሎ ሁኔታዎች እየተመቻቹለት ነው የሚል ቅሬታ አቅርቦ ነበር፡፡