የ2015 ዓ/ም የዉድድር ዘመን ላይ በተሳተፉበት የዉድድር እርከኖች ላይ ሻምፒዮን ለሆኑት ለወንዶቹ ለዋናዉ እና ከ17 ዓመት በታች ለሆነዉ ቡድን እንዲሁም ለሴቶች ቡድኑ የእዉቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የእዉቅና እና የሽልማት መርሀ ግብሩ ላይ የባህል እና ስፖርት ሚንስትር ደኤታ አንባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በ2015 ዓ/ም የዉድድር ዘመን በወንዶች ከፍተኛ ሊግ በምድብ ለ ሻምፒዮን በመሆን ወደ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላደጉት ለወንዶች ቡድን እንዲሁም በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ለሆኑት ለሴቶች ቡድን እና የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ከተማ ዉድድሮች ላይ ሻምፒዮን ለሆነዉ ከ17 ዓመት በታች ቡድናቸዉ ለእያንዳንዳቸዉ እንደተጫወቱት የጨዋታ ብዛት እና እንደሰጡት የአገልግሎት መጠን ከ650,000 ብር አንስቶ እስከ 75,000 ብር ተበርክቶላቸዋል።
- ማሰታውቂያ -
በዛሬው የሽልማት መርሀ ገብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክለቡ ተጫዋቾች አጠቃላይ ከአስራ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ሸልሟል።