የ2024/25 የወድድር ዘመን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ድልድል በዛሬው ዕለት ይደረጋል።
በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ 59 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን 5 ክለቦች በቀጥታ ወደ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ሲያልፉ ቀሪ 54 ክለቦች በመጀመሪያው ዙር የቅድመ ማጣሪያ ይገናኛሉ።
እነዚህ 54 ክለቦች በአምስት ቋቶች የተመደቡ ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመደበበት ቋት አንድ 10 የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች ተደልድለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሸነፈው እና ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ተካፋይ የሚሆነው ንግድ ባንክ ከስር ከተዘረዘሩት ክለቦች አንዳቸው ጋር ጨዋታውን ያደረጋል።
- ማሰታውቂያ -
የብሩንዲው ቪታል’ኦ
የጅቡቲው አርታ ሶላር
የኬንያው ጎር ማህያ
የሩዋንዳው ኤፒአር
የሶማልያው ዴካዳ
የደቡብ ሱዳኑ አል ሜሪክ
የታንዛኒያው አዛም
የኡጋንዳው ቪላ ጆጉ
የዛንዚባሩ ጄኬዩ
እንዲሁም የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ እና የግብፁ ፒራሚድ
ኢትዮጵያ ቡና ተካፋይ በሆነበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ደግሞ 52 ክለቦች ተካፋይ ናቸው። ከፍተኛ ውጤት ያላቸው 12 ክለቦች በቀጥታ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲያልፉ 40 ክለቦች ደግሞ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ተሳታፊ ናቸው።
ይፋ ከተደረጉት ሶስት ቋቶች መካከል ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው ቋት የሚገኝ ሲሆን በቋቱም 12 ክለቦች ተመድበዋል።
ከ16 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ዋንጫን ያሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና ከስር ከተዘረዘሩት ክለቦች አንዱ ጋር በመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ይገናኛል።
የአልጄሪያው ኮንስታንቲን
የብሩንዲው ሩኪንዞ
የኬንያው ኬንያ ፖሊስ
የሊብያ ሁለት ክለቦች(እስካሁን አልተለዩም) የሩዋንዳው ፖሊስ
የሶማሊያው ሆርሴድ
የደቡብ ሱዳኑ ጃሙስ
የቱኒዚያው ስታዴ ቱኒዝየን
የኡጋንዳው ኪታራ
የዛንዚባሩ ኡሀምያጂ
የቻምፕየንስ ሊጉም ሆነ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከነሐሴ 10 – ነሐሴ 12 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከነሐሴ 17 – ነሐሴ 19 ባሉት ቀናት ይደረጋሉ።
በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኘው የካፍ ዋና ፅ/ቤት የሚደረገው ድልድል ቀን 9:00 ጀምሮ ይከናወናል።