ዛሬ ረፋድ 4:00 ላይ በተደረገ የ23ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና አዲስአበባ ከተማ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።
በወራጅ ቀጠናዉ ላይ ይገኙ የነበሩት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ገና ከመጀመሪያው ደቂቃ አንስቶ ማሬኪ እንቅስቃሴን አስመልክቶናል በተለይ በግራ መስመር በኩል ኤልያስ አህመድ ያሻገረዉን ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ፍፁም ጥላሁን በጭንቅላቱ ወደ ግብ ሞክሮ ነበረዉን ተከላካዩ እንደምንም አዉጥቶታል። በድጋሚ በ23ኛዉ ደቂቃ ኤልያስ አህመድ በቀኝ መስመር በኩል ተጫዋቾችን ቀንሶ ወደ ድሬዳዋ የግብ ክልል ከደረሰ በኋላ ወደ ግብ የሞከራትን ኳስ ግብ ጠባቂዉ ፎሬዉ አዉጥቷታል።
በድሬዳዋ ከተማዎች በኩል ምንም እንኳን ይህ ነዉ የሚባል የተሻለ የግብ ሙከራን ከአጋማሹ በፊት ማድረግ ባይችሉም ጨዋታዉን ተቆጣጥረዉ በመጫዎት ወደ ተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል ለመድረስ ሲታትሩ ተስተዉሏል።
- ማሰታውቂያ -
በአንፃሩ ተደጋጋሚ የድሬዳዋ ከተማን የግብ ክልል ሲፈተሹ የነበሩት አዲስአበባ ከተማዎች የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ የ1 ደቂቃ እድሜ ሲቀረዉ ሌላ ድንቅ የግብ ሙከራ አድርገዋል። የድሬዳዋ ተከላካዮች ነሰሩትን ጥፋት ተከትሎ የተገኘዉን ቅጣት ምት አምበሉ ሮቤል ቀጥታ ወደ ግብ ልኳት የነበረ ቢሆንም እንደምንም ገብ ጠባቂዉ ፍሬዉ አዉጥቷታል።
በዚህ መንገድ የቀጠለዉ የሁለተለ ክለቦች ጨዋታም ግብ ሳይስተናገድበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
ከእረፍት መልስ ይበልጥኑ ተጠናክረው የገቡት አዲስአበባዎች በ61ኛዉ ደቂቃ መሪ ያደረገቻቸውን ግብ አግኝተዋል። በዕለቱ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረዉ ጋናዊው ሪችሞንድ ኦዶንጎ ከቅጣት ምት የሻገረዉን ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል።
ከዚች ግብ መቆጠር በኋላ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ያሰቡት ድሬዳዋዎች ሙሉ ለሙሉ ባላቸዉ አቅም ለማጥቃት ጥረት ሲያደርጉም ነበር ፤ በዚህም ከተከላካዩ መሳይ ጳዉሎስ በረጅም የተሻገረዉን ኳስ አብዱራህማን ሙባረክ አግኝቷት የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ በፍጥነት ተቆጣጥሯታል። በ75ኛዉ ደቂቃ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማዉ አጥቂ ቢኒያም ጌታቸዉ ከግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ ከግብ ጠባቂዉ ጋር ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ተጭነዉ የተጫወቱት ድሬዳዋ ከተማዎች በመጨረሻም በልማደኛዉ አጥቂ ሔኖክ አየለ አማካኝነት የአቻነቷን ግብ በ94ኛዉ ደቂቃ ላይ አግኝተዋል። ከማዕዘን የተሻማዉን ኳስ አጥቂዉ ሄኖክ ከመሬት ጋር አጋጭቶ ወደ ግብ በመቀየር ክለቡን አቻ ማድረግ ችሎ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም ከማራኪ ፉክክር ጋር በዚህ ዉጤት ተገባዷል።