መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ ያለበትን ውጤት አስመዝግቧል !!
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ ያለበትን ውጤት አስመዝግቧል !!

አጋራ
አጋራ

 

ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ በሀያኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ኢትዮ ኤሌትሪክን በመርታት ወደ ድል ተመልሰዉ የነበሩት አዳማ ከተማዎች ምሽት ላይ በተደረገዉ የ21ኛዉ ሳምንት መርሐግብር በወራጅ ቀጠናዉ ላይ የሚገኘዉን ሲዳማ ቡና 3ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችለዋል።

ከጨዋታዉ የመጀመሪያ ደቂቃ አንስቶ የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱን በመዉሰድ ተጋጣሚ ቡድን ላይ ገና በጊዜ ጫና ማሳደር የጀመሩት አዳማዎች በጨዋታው መባቻ ላይ በ7ተኛዉ ደቂቃ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም የፊት መስመር ተጫዋቹ አድናን ረሻድ ከአዳማ የቀኝ ማጥቃት በኩል ከዮሴፍ ታረቀኝ የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።

ከግቧ መቆጠር በኋላም አዳማዎች የሜዳዉ መሐል ክፍል ላይ በቁጥር በርከት ብለዉ በመገኘት በአንድ ሁለት ቅብብል አልፎ አልፎም በመስመር በኩል ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ሲጥሩ በተቃራኒው በግዜ ግብ የተቆጠረባቸዉ ሲዳማዎች ደግሞ በሁለቱ የመስመር ተጫዋቾቻቸው በኩል ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ ተስተውሏል።

ተደጋጋሚ ጊዜ የአዳማ ከተማ የግብ ክልል ውስጥ ቢደርሱም የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ግን ሲቸገሩ የነበሩት እና ሳጥን ዉስጥ አይናፋር የነበሩት ሲዳማዎች መደበኛዉ 45 ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት ላይ ሁለተኛ ግብ አስተናግደዋል። በዚህም የመሐል ሜዳዉ ተጫዋች አማኑኤል ጉበና ከመስዑድ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡ አጋማሹን ሁለት ለዜሮ እየመራ ወደ መልበሻ ክፍል እንዲያመሩ ማድረግ ችሏል።

ከዕረፍት መልስ አሁንም የማጥቃት ሀይላቸዉን አጠንክረዉ ወደ ሜዳ የተመለሱት አዳማዎች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ ሶስተኛ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በ64ተኛዉ ደቂቃ ላይ አሜ መሐመድ ላይ ጥፋት መሰራቱን ተከትሎ በአዳማ የግራ ማጥቃት በኩል የተገኘዉን ቅጣት ምት ወጣቱ የመስመር ተጫዋች ዮሴፍ ታረቀኝ ወደ ግብነት በመቀየር የክለቡን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችሏል።

ሶስተኛ ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ ወደ ጨዋታዉ የሚመልሳቸዉን ግብ ለማስቆጠር በርከት ያሉ የማጥቃት ባህሪ ያላቸዉን ተጫዋቾች ቀይረዉ ወደ ሜዳ ማስገባት የቻሉት ሲዳማዎች ከአስር ደቂቃዎች በኋላ በ74ተኛዉ ደቂቃ ላይ በፊት መስመር ተጫዋቹ አቤል እንዳለ አማካኝነት የማስተሳዘኛ ግብ ማግኘት ችለዋል። በቀሪ ደቂቃዎች ሁለቱም ክለቦች ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ለግብ የቀረቡ መከራዎችን ማድረግ ቢችሉም በጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳይስተናገድበት በአዳማ ከተማ 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ዉጤቱን ተከትሎም ተከታታይ ድል ያስመዘገበዉ አዳማ ከተማ በ30 ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በተቃራኒው በምሽቱ ጨዋታ ሽንፈት የገጠመዉ ሲዳማ ቡና ደግሞ በ21 ነጥቦች አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...