በስምንተኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ቀን ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ተጋጣሚውን አዳማ ከተማ 2ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።
የጨዋታዉን የመጀመሪያ አስር ያህል ደቂቃዎች ተመጣጣኝ የኳስ ፍክክር በተስተዋለበት ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ተቆጣጥረው እና በመስመሮች በኩል በሚገኙ ክፍቶች ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ሲጥሩ ሲስተዋል የነበረ ሲሆን በዚህም አዳማ ከተማ በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የሚችሉበትን ዕድል ቢያገኙም መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል። በዚህም ከተከላካይ ክፍሉ የተሻገረለትን ኳስ ከተቆጣጠረ በኋላ ግብ ጠባቂዉን አታሎ ማለፍ ቢችልም ኳሷ በመርዘሟ ሞክንያት ጥሩ ግብ የማግባት ዕድል አምክኗል።
በይበልጥኑ ወደ ራሳቸዉ የግብ ክልል አፈግፍገዉ በመጫወት አልፎ አልፎ የሚገኙ ኳሶችን በረጃጅሙ ለፊት መስመር ተጫዋቾቻቸዉ በመላክ ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ የነበሩት የጦና ንቦቹ በ20ኛዉ ደቂቃ ላይ ድንቅ ሙከራን ማድረግ ችለዋል። በዚህም ከአበባየሁ ሀጂሶ የተቀበለዉን ሷስ ቀልኪዳን ዘላለም ግብ ጠባቂዉን አልፎ ቢሞክርም ኳሷ ኢላማዋን ሳቶጠብቅ ወደ ዉጭ ወጥታለች።
- ማሰታውቂያ -
አሁን ተጭኖ በመጫወቱ እና ሙከራ በማድረጉ ረገድ የተሻሉ የነበሩት አዳማዎች በ22ኛዉ ደቂቃ ላይ በአድናን ረሻድ አማካኝነት ጥሩ ግብ የማግባት እድል ቢያገኙም ተጫዋቹ የሞከራት ኳስ የግቡን አናት ታካ ወደ ዉጭ ወጥታለች።
የመጀመሪያዉ አጋማሽ ለጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ግን አዳማዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማግኘት ችለዋል። በዚህም በ45+ ደቂቃ ላይ ከመሀል ክፍል የተቀበለዉን ኳስ ዊሊያም ሰለሞን አመቻችቶ አቀብሎት ቦና አሊ ኳሷን ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከዕረፍት መልስ በመጠኑ ተሻሽለው ወደ ሜዳ የተመለሱት ወላይታ ዲቻዎች በራሳቸዉ የግብ ክልል አፈግፍገዉ ሲጫወቱ ከነበሩበት መንግድ አጨዋወታቸውን ቀይረዉ ተጭነዉ በመጫወት የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ ፤ በዚህም በ61ኛዉ ደቂቃ ላይ አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በተጠቀሰው ደቂቃም ዮናታን ኤልያስ የበረኛዉን መዉጣት ተከትሎ ያገኛትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።
ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ የጦና ንቦቹ ዳግም መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በ65ኛዉ ደቂቃ ላይ የአዳማ ከተማዉ ተከላካይ እዮብ ማቲዎስ ሳጥን ዉስጥ ኳስ በእጅ መንካቱን ተከትሎ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ቃልኪዳን ዘላለም ወደ ግብነት ቀይሮ የክለቡን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ማድረገ ችሏል።
ጨዋታዉ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች በቀሩት ወቅትም ኢዮብ ማቲያስ ድንቅ ሙከራን ማድረግ ስሲችል ግብ ጠባቂዉ ወንድወሰን እና አናጋዉ ባደግ እንደምንም ኳሷን አዉጥተዉታል።
ከግቡ መቆጠር በኋላ ከመምራት ወደ መመራት የተሸጋገሩት አዳማዎች በርካት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ በማስገባት ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸዉ ቀርቶ በፀጋየ ኪዳነማርያሙ ወላይታ ዲቻ 2ለ1 በሆነ ዉጤት ተሸንፏል።