መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኞችን አሳውቋል
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኞችን አሳውቋል

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኞችን አሳውቋል

የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ምክትሎች በዛሬው ዕለት ይፋ ሲደረጉ የቀድሞ የክለቡ ዝነኛ ተጫዋቾች ታፈሰ ተስፋዬ የቡድኑ ምክትል ቡድን መሪ ሆኗል ።

ታፈሰ ተስፋዬ በተጫዋችነት ዘመናቸው በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ልብ ውስጥ መቀመጥ ከቻሉት ውስጥ አንዱ ሲሆን አሁን ደግሞ በሌላ ሚና ቡናማዎቹን ዳግም ተቀላቅሏል ።

ከታፈሰ ተስፋዬ በተጨማሪም ክለቡ የሁለት ምክትል አሰልጣኞች እና የአካል ብቃት አሰልጣኙንም ይፋ አድርጓል ።

ከ1988 – 1991 በኢትዮጵያ ቡና ማልያ መጫወት የቻለው እና ከ2009 አንስቶ እስካሁን ድረስ የክለቡን ከ20 ዓመት በታች ቡድንን ይዞ የነበረው አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እንዲሁም በስደስት ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው እና በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር አብሮ መስራት የቻለው አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ የክለቡ ምክትል አሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል ።

ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለው ከእንግሊዝ የመጣው የአካል ብቃት አሰልጣኙ ሚካኤል ሀይሉ ሲሆን ቡድኑን በቅድመ ውድድር ወቅት በስነ ልቦና እና በአካል በቃት ለማገዝ ቡድኑን እንደተቀላቀለ ክለቡ በይፋዊ የማህበራዊ ገፆቹ ገልጿል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...