መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ሪፖርት | በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ 3ነጥቡን ማስመዝገብ ችሏል።
ኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ 3ነጥቡን ማስመዝገብ ችሏል።

አጋራ
አጋራ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ(ቅዳሜ) 11:30 ሲል ኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና ሳሙኤል ሳኑሚ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ጣፋጭ 3ነጥብ ማግኘት ችሏል።

ብዙም ማራኪ እንቅስቃሴ ባልታየበት እና ረጃጅም ኳሶች በተስተዋለበት በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ መከላከያ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ የጨዋታ ብልጫ መውሰድ ቢችልም ያገኙአቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም ባለመቻላቸው ለመሸነፍ ተገዷል።

ጨዋታው እንደተጀመረ በ1ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያው መስፍን ኪዳኔ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ አናት ላይ ወጥቷል። ከዚህ ሙከራ 2ደቂቃ በኀላ የኢትዮጵያ ቡናው ኤልያስ ማሞ ከሳጥን ውጪ የመታው ኳስ ወደ ውጭ ወጥቷል። በመጀመሪያው 15 ደቂቃዎች በመከላከያ ግራ ክንፍ ያዘነበለው ጨዋታ በመስፍን ኪዳኔ ተደጋጋሚ ጫና ለመፍጠር ሲሞክር ነበር። 9ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ የመታው ግሩም ቅጣት ምት በግቡ አናት ላይ ወጥቷል።
36ኛው ደቂቃ ላይ ምንይሉ ወንድሙ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታውን ኳስ የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ሀሪትሰን በድንቅ ሁኔታ አውጥቶበታል። 38ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው ማናዬ ፋንቱ በግሩም ሁኔታ የሞከረው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትማ ተመልሳለች።

ከመጀመሪያው አጋማሽ እጅግ ተቀዛቅዞ የጀመረው ሁለተኛው አጋማሽ ይሄ ነው የሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴ ያልተስተዋለበት ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች አልፎ አልፎ ወደ ግብ ለመድረስ ሙከራ አድርገዋል። ይህንንም ተከትሎ 58ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ ከመከላከያው ግብ ጠባቂ ጋር ብቻ ለብቻ ተገናኝቶ የሞከራት ኳስ የግቡን ቋሚ ታካ ወጥታለች። መሱድ መሀመድ ተቀይሮ ከገባበት ደቂቃ ጀምሮ መሻሻል ያሳዩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ጨዋታው ሊጠናቀቅ 5ደቂቃዎች ሲቀሩት ሳሙኤል ሳኑሚ ባስቆጠራት ግብ አሸናፊ መሆን ችለዋል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኀላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የመከላከያ አሰልጣኝ ሻ/ል ምንያምር ፀጋዬ “ቡድናችን ቶሎ ቶሎ ወደ ጎል መድረስ ችሏል ግን ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም። ኢትዮጵያ ቡና ግን በአግባቡ መጠቀም ችሏል። መጀመሪያ ላይ ግብ ማስቆጠር ባለመቻላችን እና እንደምንፈጥረው እድል ግብ አለማግባታችን ዋጋ እያስከፈለን ነው።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ቡናው አዲሱ አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒች በበኩላቸው “እውነቱን ለመናገር ጨዋታው ከባድ ነበር። እንደዚህም ይከብዳል ብዬ አልጠበኩም ነበር። ዛሬ መሀል ሜዳ ላይ ተጫዋቾቼ ይሰሯቸው የነበሩት ስህተቶች በልምምድ ወቅት ያላየኀቸው ነበሩ። ተጋጣሚያችን ከኛ የተሻለ ብዙ ግብ የማግባት አጋጣሚ አግኝተው እኛ በማስቆጠራችን እድለኛ ነን። እንዲሁም ዋናው ነገር የምንፈልገውን 3ነጥብ ማግኘታችን ነው።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...