መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ጎል አሸነፉ!
ሀዋሳ ከተማሸገር ከተማኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ጎል አሸነፉ!

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ሸገር ከተማ ሀዋሳ ከተማን እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን በተመሳሳይ 2-1 አሸንፈዋል።

ሸገር ከተማ 2–1 ሀዋሳ ከተማ

በመጀመሪያ አጋማሽ በዙም ሳብ ያልነበረ ጨዋታ ነበር። የሸገር ከተማው ቡልቻ ሹራ ያደረገው ሙከራ የግቡን አግዳሚ ብረት መትቶ የወጣችው ኳስ በአጋማሹ ተጠቃሽ ዕድል ነበር። በዚህም የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለ ግብ ተጠናቋል።
ከዕረፍት መልስ ሸገር ከተማ የበለጠ ጫና በመፍጠር በ56ኛው ደቂቃ ካሌብ በየነ ያቀበላትን ኳስ ኦዳ መሀሙድ በግንባሩ በመግጨት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጠረ። ሸገር ከተማ ጫናዋን በመቀጠል ቢንያም ፍቅሩ በሚያምር የአጨራረስ ብቃት ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሮ መሪነቷን አስፋፋ።ሀዋሳ ከተማ ጌታነህ ከበደ አንድ ግብ በማስቆጠር ወደ ጨዋታው ለመመለስ ብትጥርም ከሽንፈት መዳን አልቻለችም። በመጨረሻም ሸገር ከተማ 2–1 በሆነ ውጤት ድል አድርጋለች።

ኢትዮጵያ ቡና 2–1 ወላይታ ድቻ

በሌላው የዕለቱ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገው ፍልሚያ ኢትዮጵያ ቡና በመጀመሪያዎቹ ደቂቃ የታሻለ የተቀሳቀሱ ስሆን። ወላይታ ድቻ በበኩላቸው ከደቂቃ ወደ ደቂቃ ወደ ጨዋታ ተመልሰዋል የተሻለ እንቅስቃሴ ማርግ ችለዋል።የመጀመሪያ የግብ ውጤት ሳይመዘገብ በ0–0 ተጠናቋል። ከዕረፍት መልስ ጨዋታው የበለጠ ፈጣን ሲሆን በ58ኛው ደቂቃ አብዱልከሪም ወርቁ ያመቻቸውን ኳስ ታይባ ምቦኑዩምዋሚ በመጠቀም ኢትዮጵያ ቡናን መሪ አደረገ። በ66ኛው ደቂቃ ታይባ ወደ ግብ ያሻማትን ኳስ የወላይታ ድቻው ተከላካይ ያኦቪ ጆሴፍ በራሱ ግብ ላይ በማስቆጠር ቡና ሁለተኛውን ግብ አገኘች።ወላይታ ድቻ በ68ኛው ደቂቃ ከማዕዘን ምት የተገኘውን ኳስ ኪሩቤል አበበ በግንባሩ በመግጨት አንድ ግብ ቢያስቆጥርም የእኩልነት ግብ ማስቆጠር አልቻለችም። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና 2–1 በሆነ ውጤት ድል በማድረግ ሶስቱን ነጥቦች አሳክታለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...