መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና ሲዳማ ቡና ነገ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታውን ያደርጋል
ሲዳማ ቡናካፍዜናዎች

ሲዳማ ቡና ነገ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታውን ያደርጋል

አጋራ
አጋራ

ሲዳማ ቡና የመጨረሻ ልምምዱን ከነገው ጨዋታ በፊት ሰርቷል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን በመወከል እየተካፈለ የሚገኘው ሲዳማ ቡና በመድረኩ የሁለተኛ ዙር ጨዋታውን ነገ በድሬዳዋ ስታዲየም ከሱዳኑ አልሂላል ኦምዱርማን ጋር ይጫወታል። በመጀመሪያው ዙር የቻዱን ኤግሎንስን በደርሶ መልስ በመርታት ያለፈው የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹው ሲዳማ ቡና ነገ ደግሞ በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ያከናውናል።

ያለፉትን አራት ቀናቶች በድሬዳዋ ልምምዱን ሲሰራ የቆየው ሲዳማ ቡና ነገ አስር ሰዓት ሲል ከሱዳኑ አልሂላል ኦምዱርማን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን መስራት የቻለ ሲሆን አምበሉ ያሬድ ባዬ በጉዳት ከወሳኙ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ሲረጋገጥ የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሠም ወደ ድሬዳዋ ከቡድኑ ጋር ቢያመራም በጉዳት መሰለፉ አጠራጣሪ ሆኗል። በአማካይ እና በመስመር ተጫዋችነቱ የምናውቀው ቢኒያም በላይ በበኩሉ ለጥቂት ቀናት ወደ ካናዳ አምርቶ በነበረበት ወቅት በቻድ ቆይታው በኢቦላ ተጠርጥቶ ማቆያ በመግባቱ ከነገው ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

ነገ ዕሁድ በድሬዳዋ ስታዲየም 10 ሰዓት ሲል የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሲደረግ ብሩንዲያዊው የ41 አመት ዳኛ ፓስፊኩዊ ንዳቢሀዌኒማና በመሐል ዳኝነት የሚመራው ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...