መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር 1–1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።
ሀዋሳ ከተማኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር 1–1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በቀይ ካርዶች የታጀበው የሀዋሳ ከተማና የኢትዮጵያ መድን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ!

በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር 1–1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።ጨዋታው ከመጀመሪያው አጋማሽ የሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂ አዲቢዬ ማርሴል ከሳጥን ውጪ በእጁ ኳሱን በመንካት ግልጽ የግብ ዕድልን በማቋረጡ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ይህም ሀዋሳ ከተማን ቀሪውን ጨዋታ በአንድ ተጫዋች ቁጥር በማነስ እንዲያከናውን አስገድዷል።የተጫዋች ቁጥር ብልጫውን የያዘው ኢትዮጵያ መድን በ23ኛው ደቂቃ አልፍሬድ ኩሩንዚዛ ባስቆጠረው ግብ መሪነቱን ወስዷል። ሆኖም ሀዋሳ ከተማ በቀላሉ እጅ ሳትሰጥ የአቻነት ግብ ፍለጋ ጥረቷን ቀጥላለች።ጥረቷም በ62ኛው ደቂቃ ፍሬ አፍርቷል። ጌታነህ ከበደ ከፍጹም ቅጣት ምት ያገኘውን ዕድል ወደ ግብ በመቀየር የጨዋታውን ውጤት ወደ 1–1 አምጥቷል።የጨዋታው ውጥረት በዚህ ብቻ አልተገታም፤ የኢትዮጵያ መድኑ ዋንጫ ቱትም በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ ጨዋታውን ይበልጥ አጓጊ አድርጎታል።በመጨረሻም ሁለቱ ቡድኖች የድል ግብ ሳያስቆጥሩ በ1–1 ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል። በዚህም በቀይ ካርዶች፣ በግቦችና በተጋድሎ የታጀበው ፍልሚያ ሁለቱንም ቡድኖች አንድ አንድ ነጥብ አጋርቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...