መነሻ ገጽ ካፍ ወላዋሎ የሜዳ ጨዋታው ሰርዞ ወደ ሊቢያ ወስዷል
ካፍኮንፌድሬሽን ካፕወልዋሎዜናዎች

ወላዋሎ የሜዳ ጨዋታው ሰርዞ ወደ ሊቢያ ወስዷል

አጋራ
አጋራ

ወልዋሎ የኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሁለተኛው ዙር የሜዳ ጨዋታውን በሊቢያ ለማድረግ መወሰኑና አሳወቀ።

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው ክለባችን ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ሂላል አል ሳህልን አሸንፎ ወደ የሚቀጥለው ዙር በማለፍ በሁለተኛው ዙር ከሊብያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጋር መደልደሉ ይታወሳል።

ቀድሞ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ጥቅምት 6 በድሬዳዋ ስታዲየም ፣ ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም በሊቢያ ትሪፖሊ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አስገዳጅ በሆነ ምክንያት ክለቡ በሜዳው ድሬዳዋ ማድረግ የነበረበትን ጨዋታ ወደ ሊብያ ለመቀየር መገደዱን ክለቡ አሳውቋል።

ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በባለ ሀብቶች ድጋፍ ሲንቀሳቀስ እስከ አሁን እንደቆየ የተሰማው ክለቡ ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ እንዲካሄድ በነበረው ከፍተኛ ፍላጎት እና ፅኑ አቋም ለዓዲግራት ከተማ አስተዳደር እና ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የበጀት ጥያቄ አቅርቦ ቀደም ሲል ተጋጣሚውን የሜዳችሁን ጨዋታ በእኛ ሜዳ አድርጉ በማለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ቢያደርግም በትግራይ ክልል ባለው አሁናዊ ሁኔታ ይህ ነው የሚባል በጀት ማግኘት ክለቡ አልቻለም።

ይህንንም ተከትሎ በቅርብ ዓመታት በበጀት እጥረት ምክንያት ያጋጠሙትን ስፍር ቁጥር የሌላቸውና ያንገዳገዱንን ችግሮች ላለመድገም እና የቀረበውን ውል ከግምት ውስጥ በማስገባት መሸካካሻ ክፍያ ፣ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ገቢ ፤ የስታዲየም ገቢ እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማዳበር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ቀጣይነት ያለው ትብብር በማድረግ ቡድናችንን ለመደገፍ በተካተቱበት ውል በሜዳችን ጥቅምት 6/2019 ማድረግ የነበረብንን ጨዋታ በሊቢያ ለማከናወን ወስነናል ሲል ክለቡ ይፋ አድርጓል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...