ሀድያ ሆሳዕና ናይጄሪያዊውን የመሐል ተከላካይ በይፋ አስፈርሟል።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝ የቀጠረው እና ወደ ልምምድ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱን የቋጨው ሀድያ ሆሳዕና 26 አመቱ እንደሆነ የተነገረለትን ናይጄሪያዊውን የመሐል ተከላካይ አፎላያን ፒተርስ በይፋ አስፈርሟል።
በሀገሩ ክለቦች ዲኖ ፣ ህርት ላንድ እና እንዲሁም በናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ ከ38 ጨዋታዎች በ35 በተሰለፈበት ኢንይባ አባ በተባለው ክለብ የተጠናቀቀውን አመት ቆይታ ካደረገ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው ሀድያ ሆሳዕና በአንድ አመት ውል ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ