በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ከከፍተኛ ሊጉ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች በዛሬው ዕለት የቀድሞው የነገሌ አርሲ እና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለፉትን አመታትን ቆይታ ያደረገው እና በክለቡ የአንድ አመት ኮንትራት እየቀረው በስምምነት የተለያየው ግብ ጠባቂው አሸብር ተስፋዬ ፣ የቀድሞው የቦዲቲ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት አመታት በወላይታ ድቻ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው አማኑኤል አሊሴ እና በመቻል እና የተጠናቀቀውን አመት በከፍተኛ ሊጉ ሻሸመኔ ከተማ ያሳለፈው አጥቂው ሙሀባ አደም በይፋ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅለዋል።
አስተያየት ይስጡ