ፋሲል ገብረሚካኤል ወደ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።
ከደደቢት ከተነሳ በኋላ በሰበታ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያ መድን መጫወት የቻለው እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቆይታን ማድረግ የቻለው ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል ወደ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ለማምራት ከስምምነት የደረሰ ሲሆን ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለው ኮንትራት ከዚህ ወር በኋላ ሲገባደድ በይፋ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚካፈለውን ቡድን እንደሚቀላቀል ያገኘውት መረጃ ያመላክታል።
ሴኔጋላዊውን የግብ ዘብ አማር ፎሎን ያስፈረመውን እና የናትናኤል ኪዳኔን ውል ያደሰው ክለቡ ተጨማሪ ግብ ጠባቂ በማስፈረም ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ