የጣናው ሞገድ የፊት አጥቂውን አንተነህ ተፈራን ውል አራዝሟል
በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ለትውልድ ሀገሩ ሻኪሶ ሲጫወት ባሳየው አቋም ወደ ኢትዮጵያ ቡና በማምራት ከብዙሀኑ ጋር ለመተዋወቅ የበቃው የመስመር እና የፊት አጥቂው አንተነህ ተፈራ የተጠናቀቀውን አመት በሸገር ከተማ ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ከጣናው ሞገድ ጋር ቀሪ የስድስት ወራት ውል ቢቀረውም ተጨማሪ አንድ አመት ለመቆየት ውሉን በክለቡ አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ