ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል ከፍተኛ ገንዘብ የጠየቀው ሴኔጋላዊ በመጨረሻም በባህርዳር ይቆያል።

የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል መሸለም የቻለው የቀድሞ የሀድያ ሆሳዕና ግብ ጠባቂ ፔፕ ሰይዶ ያለፉትን ሦስት አመታት ካሳለፈበት ባህርዳር ከተማ ወደ ሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና ለማምራት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የጠየቀው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ለተጨማሪ አንድ አመት ባለበት ክለብ ባህርዳር ከተማ መቀጠሉ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ