ኢትዮጵያዊት የትዳር አጋር ያገኘው ዩጋንዳዊውን አጥቂ ውሉን ሲያራዝም ወጣቱ ተጫዋችም ክለቡን ተቀላቀለ።
ወደ ዝውውሩ ጠለቅ ብለው የገቡት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የዩጋንዳዊውን አጥቂ ሳይመን ፒተርን ውል ሲያድሱ ወጣቱን ተጫዋች የግላቸው አድርገዋል።

በባህርዳር በነበረው የጣና ዋንጫ የሀገሩን ክለብ ቡልን ለቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሦስት ቆይታን ያደረገው እና ኢትዮጵያዊት የትዳር አጋር በሀገራችን ባህል ያገባው ዩጋንዳዊው አጥቂ ሳይመን ፒተር በንግድ ባንክ ውሉን አድሷል።
በአብዲ ቦሩ እና ፉሪ ክፍለ ከተማ እጅግ አስደናቂ ቆይታን በአንደኛ ሊጉ ማሳየት የቻለው ወጣቱ ተከላካይ ፉዓድ እድሪስ ክለቡን የተቀላቀለው አዲሱ ፈራሚ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ