ንግድ ባንክ የወሳኝ ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር እና የአራት ነባሮችን ውል ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ሦስት አመታት በክለቡ ቆይታን እያደረጉ የሚገኙትን የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ፣ ገላን እና ኢትዮጵያ መድን አማካይ የነበረውን ቢኒያም ካሳሁን እና የቀድሞው የኢኮስኮ ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ባህርዳር ከተማ የግራ መስመር ተከላካይ የነበረውን ተስፋዬ ታምራትን ውል ማራዘሙ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ