ኢትዮጵያ ቡና አምስተኛው ፈራሚው የመስመር አጥቂው ሆኗል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች እስከ አሁን በዝውውሩ አቡበከር ኑራ ፣ በረከት ወልደዮሐንስ ፣ አብዱሰላም የሱፍ እና ሀብታሙ ተከስተን በይፋ የስብስባቸው አካል ማድረግ የቻሉ ሲሆን አሁን ባጣራውት መረጃ መሠረት የህክምና ምርመራውን በማድረግ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አምስተኛው ፈራሚ የመስመር አጥቂው ዳዊት ገብሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ።

ባለፉት ሁለት አመታት በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አስደናቂ ብቃቱን ያስመለከተን ይህ ተጫዋች ለኢትዮጵያ ቡና ለሁለት አመታት ለመጫወት ስምምነት ፈፅሞ ክለቡን ስሙን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን መላኩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
አስተያየት ይስጡ