የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪው ወላይታ ድቻ የግብ ዘቡን ሦስተኛ ፈራሚ አድርገውታል።
በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመሩት እና የቴዎድሮስ ታፈሠ እና መሳይ ኒኮልን ውል ካደሱ በኋላ በዛሬው ዕለት ሀሰን በሽር እና በረከት ወልዴን በማስፈረም ዘደ ዝውውሩ የገቡት ወላይታ ድቻዎች ሦስተኛው ፈራሚያቸው ወጣቱ ግብ ጠባቂ ምንታምር መለሠ ሆኗል።

በሺንሺቾ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ላለፉት ሁለት አመታት በመቻል ያሳለፈው የግብ ዘቡ የጦና ንቦቹን በሁለት አመት ውል መቀላቀሉን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ