በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ የሚመራው መቻል ወደ ዝውውር ገብቷል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአሰልጣኝ መሠረት ማኔው መቻል ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ነባሮችን ውል አድሷል።

በመቻል ቤት ላለፉት ስድስት አመታት እየጫወተች የምትገኘው የቀድሞዋ የሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካይ ነፃነት ፀጋዬ በአዳማ እና መቻል የምናውቃት የተከላካይ አማካዩዋ ፂዮን ፈየራ ፣ የቀድሞዋ የአርባምንጭ ፣ ሀዋሳ አቃቂ እና መቻል አማካይ የነበረችው ቱፊት ካዲዮ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿ ትዕግስት ብርቄ ለቀጣይ ሁለት አመታት በመቻል ለመቆየት ውላቸውን አራዝመዋል።
ውል ካራዘሙ ተጫዋቾች በተጨማሪ ክለቡ የቀድሞዋን የክለቡ የቀኝ መስመር ተከላካይ ፀሀይነሽ ጁላን ከሀዋሳ ከተማ እና በአቃቂ ፣ አርባምንጭ ሀዋሳ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበራት አማካዩዋ ዙፋን ደፈርሻ አዲሶቹ የመቻል ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል።
አስተያየት ይስጡ