ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ ሎዛ አበራ በአሜሪካው ክለብ ለተጨማሪ አመት ውሏን አራዝማለች።

እግር ኳስን በክለብ ደረጃ 2004 ላይ በሀዋሳ ከተማ የጀመረችው እና በሀገር ውስጥም ለደደቢት ፣ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጫወት የደመቀችው ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ ሎዛ አበራ በሆላንድ እና በተለይ በማልታው ክለብ ቢርኪርካራ የነበራትን የፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወት ልምድ በመጠቀም ላለፉት ሁለት አመታት በአሜሪካ የታችኛው የሴቶች ሱፐር ሊግ ተካፋዩ ዲሲ ፓወር ክለብ ውስጥ ሁለት አመታትን ቆይታ ማድረጓ ይታወሳል።
እስከ በክለቡ ባደረገቻቸው 47 ጨዋታዎች 12 ግቦችን በማስቆጠር 4 ወደ ጎልነት የተቀየሩ ኳሶችን ማቀበል የቻለችው አጥቂዋ ሎዛ አበራ ለተጨማሪ አንድ አመት በቡድኑ ውስጥ ውሏን አራዝማለች።
አስተያየት ይስጡ