ለእንግሊዙ ፕለይ ማውዝ የሚጫወተው የታዬ አሽቢ ታናሽ ወንድምን እናስተዋውቃችሁ።

ቀደም ባለው ፅሁፌ ከፉልሀም አካዳሚ ስለተገኘው ታዬ አሽቢ ሀሞድ ነግሬያችሁ የነበረ ሲሆን በአሁን ፅሁፌ ደግሞ ታላቅ ወንድሙን አርዓያ በማድረግ ስላደገው የ25 አመቱ ሉካ አሽቢ ሀሞድ ልንገራችሁ። በእንግሊዝ ምድር ውልደቱን ያደረገው እና እንደ ወንድሙ ሁሉ የእግር ኳስ መነሻውን መነሻውን በክራባን ኮቴጁ ፉልሀም ስልጠናውን ማድረግ የቻለው ግብ ጠባቂው ሉካ አሽቢ ከፉልሀም በመቀጠል ለሀሮው ቦሮ ፣ ስቶክ ፖርት ፣ ክራውሊ ታውን ፣ ኖንትስ ካውንቴ እና ኦልደር ሹት በተባሉ የእንግሊዝ ክለቦች ውስጥ ቆይታውን አድርጎ በአሁኑ አሁኑ ሰዓት ደግሞ በእንግሊዝ ሦስተኛው የሊግ ዕርከን ፕለይ ማውዝ ውስጥ ግልጋሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በቀጣይ ወደ ቻምፒዮን ሺፕ ክለብ እንደሚያመራ የሚጠበቀው እና የእንግሊዝን መለያ በመልበስ ከ15 ፣ 16 ፣ 17 ፣ 18 ፣ 19 እና ከ20 አመት በታች ቡድኖች ውስጥ በተከታታይ እየተጠራ ሀገሪቷን ማገልገል የቻለ ሲሆን አሁን ግን አንድ ሜትር ከዘጠና አንድ ሴንት ሜትር የሚረዝመው የግብ ዘቡ ወደ እናቱ ሀገር ኢትዮጵያ ፊቱን ማዞሩን በተደጋጋሚ ሲገልፅ ይደመጣል።
ይህ ህልሙ ግን መቼ ይሳካ ይሆን ? ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል!
አስተያየት ይስጡ