ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊጉ ክለብ ፉልሀም መነሻውን ያደረገው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ግብ ጠባቂን እናስተዋውቃችሁ።

ከኢትዮጵያዊት እናት የተገኘው በለንደን ከተማ የተወለደው ቁመታሙ ግብ ጠባቂ ታዬ አሽቢ ሀሞንድ መጠሪያ ስሙ ነው። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በእንግሊዝ ሊግ ዋን ከሚገኙ ድንቅ ግብ ጠባቂዎች ተርታ እስከ መሆን ደርሷል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለሚገኘው የፉልሀም አካዳሚ የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኋላ አሁን ከ18 እና ከ23 አመት በታች የፉልሀም ቡድኖች ውስጥም በመጫወትበደንብ ራሱን እያበቃ በአሁኑ ሰዓት ለግብ ጠባቂዎች ወሳኝ ነው በሚባልለት 27ኛ ዕድሜው ላይም ይገኛል። ከፉልሀም በኋላ ለቺፕ ስቴድ ፣ ሜይድ ሄድ ዩናይትድ እና ቦርሀም ውድ ከተጫወተ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ከቻምፒዮን ሺፑ ቀጥሎ ሦስተኛ በሆነው የእንግሊዝ ሊግ ዋኑ ክለብ ስቴፌኔጅ ክለብ ውስጥ በመጫወት ላይ ይገኛል።

የእርሱ ግብ ጠባቂ መሆን ለታናሽ ወንድሙ ሉካ አሽቢ መሠረት መሆን የቻለው አንድ ሜትር ከዘጠና የሚረዝመው ታዬ አሽቢ ለእንግሊዝ ከ16 እና ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ የነበረውን ድንቅ ጊዜ በእናቱ ሀገር ኢትዮጵያ የመድገም ህልም እንዳለውም ይናገራል።

ስለ ታናሽ ወንድሙ ሉካ አሽቢ በቀጣይ ፅሁፍ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ