መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ በታንዛንያው ክለብ ውሉ አራዝሟል
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ በታንዛንያው ክለብ ውሉ አራዝሟል

አጋራ
አጋራ

በታንዛንያው ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ በሆነው አዛም ክለብ ውስጥ ቆይታን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ለተጨማሪ አመት ውሉን አራዝሟል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተስፋ ካላቸው ወጣት አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳል ኢትዮጵያዊው አዲስ ወርቁ የአውሮፓ ፕሮ ላይሰንስ ባለቤት ከመሆኑ በዘለለ በበርካታ አለማት በመዞር በተለይ በጀርመን ሀገር የቦንደስሊጋ ስልጠናዎችን በመውሰድ ራሱን እያሳደገ የመጣው ወጣቱ አሰልጣኝ በመቀጠል ከሰርቪያዊው ሰርዲ ሚሊት ሚቾ ጋር በዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን የቪዲዮ ተንታኝ በኋላም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2014 እና በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ሲያነሳ በክለቡ ውስጥ የቪዲዮ ተንታኝ እና ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ አገልግሏል።

በመቀጠል ወደ ሱዳኑ አልሂላል በማምራት የኮንጓዊው ፍሎረንት ኢቢንጌ ረዳት በመሆን በመስራት ባሳየው ትልቅ አቅም በያዝነውም አመት ወደ ታንዛኒያ በማምራት ከአሰልጣኙ ጋር በረዳትነት እያገለገለ ክለቡ በሊጉ ሦስተኛ ደረጃን እንዲይዝ ከፍ ያለ አበርክቶን ያደረገው ሰው በመጨረሻም የማሊ ብሔራዊ ቡድንን ይይዛሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የቀድሞው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ አር ኤስ በርካኔ እና አልሂላል አሰልጣኝ በክለቡ ውላቸውን በማራዘማቸው ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝም ለተጨማሪ አመት ውሉን በክለቡ አራዝሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...