የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የአመቱ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አማኑኤል ግዛቸው።

በጦሳ ተራራ ተከባ ዘውዷን ከደፋችሁ በአይጠየፍ አዳራሽ ስሟን ከገነባችሁ ሁሉን በዕኩል ፍቅር ዘርታ ከሚኖሩባት የወሎዎች ምድር ደሴ ከተማ ነው ውልደቱ ወጣቱ አጥቂ አማኑኤል ግዛቸው እግር ኳስን በዕትብቱ ምድር ደሴ ከተማ ክለብ ውስጥ በ2013 የውድድር ዘመን በቢጫ ተሴራ የክለብ ህይወቱን አሀዱ ብሎ ቢጀምርም በአመቱ ግን በአካባቢው በነበረው የሰላም ዕጦት ከውድድር መራቁን ተከትሎ ወደ የካ ክፍለ ከተማ በማምራት ቆይታን ማድረግ የቻለው በ2015 የውድድር ዘመን ዳግም ወደ ቀደመ ቤቱ ደሴ ተመልሶ ቆይታን ሲያደርግ በዛው አመት ከጅማ አባጅፋር ጋር በነበረ ጨዋታ ከባድ ጉዳት ገጥሞት ከሜዳ ለመራቅ የተገደደው ወጣቱ ተጫዋች በጭራሽ አይመለስም ቢባልም ከቀዶ ጥገናው አገግሞ ወደሚወደው እግር ኳስ ለመመለስ በቅቷል።
ምንም እንኳን ደሴ ከተማ ወዳለመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ከጫፍ ደርሶ ባይሳካለትም በግሉ ጥሩ አመትን ያሳለፈው ወጣቱ አማኑኤል ግዛቸው 10 ጎሎችን በማስቆጠር በደሴ ከተማ መለያ የ2018 የከፍተኛ ሊጉ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ቋጨቶ በፕሪምየር ሊግ ክለቦች ዐይን ውስጥ ከወዲሁ ገብቷል።
አስተያየት ይስጡ