መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

አጋራ
አጋራ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ።

የኢትዮጵያን ባህል ለአለም ለማስተዋወቅ ከፍ ያለ አበርክቶ ያለው የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በሚል ስያሜ በካናዳ ቶርንቶ በርካቶች በተገኙበት በይፋ ተመስርቷል። በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያን በባህል እና ስፖርት በጋራ አንድ ሆነው እርስ በእርስ እንደሚገናኙበት የሚጠበቀው ይህ የሊግ ምስረታ ከፍተኛ ልምድ እና ለሀገራቸው ጥልቅ ፍቅር ባላቸው ግለሰቦች የተመሠረተ እንዲሁም አንድነትን በይበልጥ ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅም በምስረታው ዕለት ተገልጿል።


ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያን የበለፀገ ባህል ፣ ቋንቋ እና ታሪክ ሳይዘነጋ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን እንዲማር ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባሻገር በየዓመቱ የሚካሄዱ ታላላቅ የስፖርት ውድድሮችን በማዘጋጀት ማህበረሰቡን ማሳተፍ እና ኢትዮጵያዊ ሀሳቦች እንዲያድጉ አባል ክለቦችን በመመዝገብ በስነ-ምግባር የታነ እና በቴክኒክ የበለፀገ ጠንካራ የሊግ ውድድር መዘርጋት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ ፕሬዝዳንት አቶ ማይክ ማስረሻ ሊጉ ከስፖርቱ በበለጠ ለማህበረሰቡ የጀርባ አጥንት እንዲሆን መታቀዱን ገልፀው ልጆች እየተጫወቱ ባህላቸውን እንዲያውቁ የማድረግ እና ትልልቆችም ደግሞ በመገናኘት ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ እንዲሆን እደሚሰራ ገልፀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...