መነሻ ገጽ ዜናዎች ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ ድል ሲያሳኩ የመቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታን ከ ኢትዮጵያ መድን ያገናኘ ሲሆን በንፅፅር ኢትዮጵያ መድኖች የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉ ቢመስልም በሙከራ ረገድ ግን ተመሳሳይ ባህሪን በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች አሳይተዋል። ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሲመለስ የተሻለ 67ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ሳሙኤል ሳሊሶ ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ ጋናዊው ተከላካይ እስማኤል አብዱልጋኒዮ ወደ ጎልነት ለውጦ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌውን ቡድን መሪ ማድረግ ችሏል።

የተጫዋች ለውጥን ካደረጉ በኋላ በይበልጥ በሽግግር መንቀሳቀስን የጀመሩት ሞዓም አናብስቱ 84ኛው ደቂቃ ከቀኝ የሜዳው ክፍል የተገኘውን የቅጣት ምት አሰጋኸኝ ጴጥሮስ አሻምቶ ፍሬዘር ካሳን ጨርፋ የመጣችን ኳስ ተቀይሮ የገባው ብርሀኑ አዳሙ የአቻነት ጎል በማድረግ በመጨረሻም 1ለ1 ጨዋታው ሲጠናቀቅ ውጤቱም ለመቐለዎች እጅግ አስከፊ ሆኗል።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከናወነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሸገር ከተማ መርሀግብር ሀምራዊ ለባሾቹ ከሽንፈት ወደ ድል የመጡበትን ወሳኝ ነጥብ አስመዝግበዋል። 9ኛው ደቂቃ ላይ ሳይመን ፒተር ታግሎ የሰጠውን ናትናኤል ዳንኤል ከጀርባው ለተገኘው አዲስ ግደይ ሰጥቶት ንግድ ባንክን ቀዳሚ አድርጓል። ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሲቀጥል ሸገሮች የንግድ ቤንኩ የግብ ዘብ ጊቢ ጆቤ በናትናኤል ዘለቀ ላይ ሳጥን ውስጥ በሰራው ጥፋት የተሰጠን የፍፁም ቅጣት ምት ሔኖክ አዱኛ ካመከናት ከውስን ደቂቃ በኋላ 54ኛው ደቂቃ አብዱላሂ ዲያካም ከራሱ ሜዳ በረጅሙ ያሻገረውን ኳስ ሳይመን ፒተር እንደምንም ወደኋላ ሰጥቶት ናትናኤል ዳንኤል ለንግድ ባንክ ሁለተኛ የአመቱ ደግሞ አስራ አንደኛ ጎሉ በማድረግ ጨዋታው ወደ 2ለ0 ተለውጧል።

ቀስ በቀስ የተጫዋቾችን ለውጥ በማድረግ ወደ ጨዋታ ቅኝት የገቡት ሸገሮች 78ኛው ደቂቃ ላይ ናትናኤል ዘለቀ በረጅሙ የጣለውን ኳስ የንግድ ባንኮቹ ተከላካዩ አብዱላሂ ዲያካም እና የግብ ዘቡ ጊቤ ጆቤ አለመናበባቸውን ተከትሎ ኳሱን ፈጥኖ ያገኘው ቢኒያም ፍቅሩ ወደ ግብነት ቀይሮ በመጨረሻም ጨዋታው በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ በተደረገ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ 2ለ0 በሆነ ውጤት ድሬዳዋ ከተማን አሸንፏል። ከዕረፍት በፊት 47ኛው ደቂቃ ላይ መሐመድ ኑርናስር በግራው የሜዳ ክፍል መሳን አገኘሁ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የቅጣት ምት ፍፁም ፍትህአለሙ ወደ ጎልነት ለውጧት የጣናውን ሞገድ ቀዳሚ ሲያደርግ ከዕረፍት መልስ ደግሞ 58ኛው ደቂቃ ራሱ አንተነህ ተፈራ በረጅሙ አሻግሮ በድጋሚ ወንድወሰን በለጠ መልሶ በረጅሙ የሰጠውን ኳስ ከሳጥኑ ጠርዝ አንተነህ ተፈራ እጅግ አስገራሚ ጎልን ፍሬው ጌታሁን መረብ ላይ በማስቀመጥ ጨዋታው በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድን የበላይነት ተጠናቋል።

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ከቅጣት መልሰው ማግኘት ያልቻሉት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁንም ከገቡበት የወራጅ ቦታ መውጣት አልቻሉም።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...