መቐለ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ሲያሰናብት ሌላ አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥረት ጀምሯል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ደካማ የውድድር ጉዞን እያደረገ የነበረው እና በደረጃ ሰንጠረዡ 19ኛ ላይ ለመቀመጥ የተገደደው መቐለ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ከሀላፊነት አሰናብቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በያዟቸው ክለቦች ውጤታማ መሆን እየከበዳቸው የመጡት አሰልጣኙ ባለፈውም አመት ይዘውት በተመሳሳይ ጉዞ ላይ ሲጓዙ የነበሩት እና ዘንድሮም በተመሳሳይ መንገድ ላይ ክለቡን ያደረጉት አሰልጣኙ ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ስንብት በኋላ ቡድኑን በጊዜያዊ ስያሜ ተረክበው ቢያሰለጥኑም ውጤታማ አለመሆናቸው ክለቡን ሊያሰናብታቸው ግድ ብሏል።
ክለቡ በቀጣይ የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ መቻል እና ወላይታ ድቻ ከነበሩት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን ምርጫውን ለማድረግ ጥረት መጀመሩን ሰምቻለሁ።
አሰልጣኙ ቢሾሙስ ክለቡን በሊጉ ያቆዩት ይሆን ? ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ