መነሻ ገጽ ዜናዎች ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ
ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

አጋራ
አጋራ

በዮሴፍ ከፈለኝ

በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት ሲመለሱ ቅያሪ ተጫዋች ላይ የተሳሳተው ዳኛ ግን ባላየ ታልፏል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ነገሌ አርሲ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን 2ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ውጤት ለዋጭ ስህተትን ሰርተዋል የተባሉትት ፌድራል ዋና ዳኛ አርቢትር አሸብር ሰቦቃ እና ረዳት ዳኛው ወጋየሁ አየለ እንደተለመደው ከውድድሩ ስፍራ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

በሊጉ ስህተት ሲሰራ ጩህት ለማብረድ ዳኞችን የሚመልሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ለዳኞች አቅም መዳበር ምን እየሰራ ነው የሚል ጥያቄም በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው። ያም ሆኖ መፍትሄ ካልተገኘ የቅሬታ አቅራቢ ክለቦችን ጥያቄ ለማብረድ ብቻ ዳኞችን ዞር ማድረግ መቀጠሉ የማይቀር ይመስላል። ከሰሞኑ በአንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ አራተኛ ዳኛው የሰራው ስህተትም ደግሞ በዝሞታ ታልፏል።  አራተኛ ዳኛው   እንዲቀየር ያደረገው ተጫዋች ከተባለው ውጪ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ተጫዋቹ ተቀይሮ ከወጣ በኋላ ስህተት ቢሆንም በደንቡ መሠረት የማይመለስ ሲሆን ክለቡ ጠቃሚ ተጫዋቹ በስህተት ወጥቶብኛል ብሎ ውስጥ ለውስጥ    አጉረምርሞ ብቻ በመቅረቱ እና ባለ መከሰሱ ዳኛው ከቅጣት በዝምታ ታልፏል። የዕለቱ የጨዋታ ኮሚሽነር በጉዳዩ ዙርያ ሪፖርት ይፃፉ ወይም አይፃፉ የታወቀ ነገር ባይኖርም ኮሚቴው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...