የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ይጓዙ ይሆን ? ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ ሐምሌ 4/2018 ዕለተ ቅዳሜ የወዳጅነት ጨዋታን በአሜሪካ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር እንደሚያደርግ ታውቋል። በጆ ማሞ ካቻ አመቻችነት ለሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታም የትኬት ሽያጭ መደረግ የጀመረ ሲሆን ዋልያዎቹም በሰኔ ወር አጋማሽ ዝግጅትን ማድረግ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኦዲ ፊልድ አሜሪካ በሚደረገው ውድድር ላይ በአሜሪካ ይኖሩ የነበሩት የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በግል ጉዳይ አሜሪካን ለቀው ከወጡ ከረጅም አመታት በኋላ በድጋሚ አሜሪካ የመግቢያ ፍቃድ ሰጥታቸው ብሔራዊ ቡድኑን እየመሩ ያመራሉ ወይንስ ደግሞ ብሔራዊ ቡድኑ ያለ ዋና አሰልጣኝ ያመራል የሚሉ ጉዳዮች ይጠበቃሉ።
አስተያየት ይስጡ