በተጠናቀቀው የወድድር አመት በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ በሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት ነጥቦችን ሰብስበዉ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ሀዋሳ ከተማዎች በዛሬዉ ዕለት በይፋ ወደ ዝውውሩ በመግባት ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
የመጀመሪያ ፈራሚ በመሆን ሀዋሳ ከተማ የደረሰዉ ከዚህ ቀደም ለሙገር ሲሚንቶ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሰበታ ከተማ መጫወት የቻለዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ በረከት ሳሙኤል ሲሆን በዚህም ተጫዋቹ ቀጣዮቹን ሁለት አመታት በሀይቆቹ መለያ የምንመለከተዉ ይሆናል።
ሌላኛዉ እና በዛሬዉ ዕለት ሁለተኛ ፈራሚ በመሆን ክለቡን የተቀላቀለዉ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለወላይታ ዲቻ መጫወት የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ እየብ አለማየሁ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህም ተጫዋቹ በተመሳሳይ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ለሀዋሳ ከተማ ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩ ታዉቋል።
አስተያየት ይስጡ