ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በሜዳዋ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል እና የካፍን ሚኒማ የሚያሟላ ስታዲየም ስለሌላት በሚል በሜዳዋ ማድረግ የሚገባትን ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ ማለትም በደቡብ አፍሪካ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል። ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላም ይህ ነዉ የሚባል የተሻሻለ ነገር በስታዲየሞቹ ባለመኖሩ ምክንያት ኢትዮጵያ በድጋሚ በሜዳዋ እንዳትጫወት ካፍ አግዷታል።
በያዝነዉ ወር መገባደጃ ላይ ለሚደረገዉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳዉ እንዲጫወት እና የካፍ አመራሮችን ዝቅተኛ መስፈርት እንኳን ለማሟላት ረብርብ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ መቅርቱ ታዉቋል።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን እያስተናገደ የሚገኘዉ ሜዳዉ ከዚህ ቀደሙ አንፃር የመጫወቻ ሜዳዉ ላይ እና የመልበሻ ክፍሎቹ ላይ በተቻለ መጠን ማስተካከያ ተደርጎበት ባሳለፍነዉ ሳምንት በካፍ አመራሮች ተገምግሞ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ስታዲየሙ አህጉር አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ብቁ ባለመሆኑ ምክንያት በቀጣይ የሚደረገው የኢትዮጵያ እና የግብፅ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በገለልተኛ ሀገር እንደሚደረግ ተገልጿል።
አስተያየት ይስጡ