መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

የ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የባህርዳር ከተማዉ አጥቂ ላይ በርከት ያለ የጨዋታ እገዳ የተጣለበት ሲሆን ፤ በተመሳሳይ ሌሎች ተጫዋቾች እና ክለቦች ላይም የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል !!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ረቡዕ ሚያዝያ 19 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎችን ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን በተጫዋቾች እና ክለቦች ላይ አሳልፏል።

በተጫዋቾች ደረጃ ሐይደር ሸረፋ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን 1 ጨዋታ እንዲታገድ አንዲሁም በተመሳሳይ የክለብ አጋሩ እንዲሁም ሱሌይማን ሀሚድ ፣ የቡናዉ ኃይሌ ገ/ትንሳይ ፣ የድሬዳዋ ከተማዉ ዳንኤል ደምሴ ፣ የሀዋሳ ከተማዉ ኤፍሬም አሻሞ ፣ የፋሲል ከነማዎቹ አምሳሉ ጥላሁን እና ሽመክት ጉግሳ በተለያዩ  የክለባቸው ጨዋታዎች አምስት ቢጫ ካርድ ያዩ ሲሆን ለፈፀሙት ጥፋት በቀጣይ 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።

የባህርዳር ከተማዉ አጥቂ ማዊሊ ኦሲ በ20 ኛ ሳምንት የክለቡ ጨዋታ በ92ኛው ደቂቃ ላይ ከዳኛ እይታ ውጭ የተጋጣሚ ተጫዋችን ኳስ በሌለበት ሃይል በተቀላቀለበት የቆመ እግሩን ስለመርገጡና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ አንገቱን በማነቅ ስለመገፍተሩ በዕለቱ የጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት የቀረበበት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 3000 ብር እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦች ደረጃ ሀዲያ ሆሳዕና ፣ ድሬደዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በሳምንቱ በነበራቸው ጨዋታ የክለባቸው የተለያዩ ተጫዋቾች አምስት የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ በማየታቸው እያንዳዳቸው 5000 ብር እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፏል ሲል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...