መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | አዞዎቹ በውድድር ዓመቱ ለአራተኛ ጊዜ አሸንፈዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአርባምንጭ ከተማአዲስአበባ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዞዎቹ በውድድር ዓመቱ ለአራተኛ ጊዜ አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማን ከአዲስ አበባ ከተማ አገናኝቶ በፀጋዬ አበራ ሁለት ግቦች አርባምንጭ ከተማዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዘው ወተዋል ።

አርባምንጭ ከተማ በ16ኛው ሳምንት ከመከላከያ ከተማ ጋር አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ላይ በተጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ አራት ለውጦችን በማድረግ የገቡ ሲሆን በበርናንድ ኦቼንጌ ፤ ሀቢብ ከማል ፤ መሪሁን መስቀለ እና አንዱአለም አስናቀ ምትክ ኡቸና ማርቲን ፤ ተካልኝ ደጀኔ ፤ አቡበከር ሻሚል እና በላይ ገዛኸኝ ሲያሳልፉ በአዲስ አበባ ከተማ በኩል በሳምንቱ ከባህርዳር ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ አሰጋኸኝ ጴጥሮስን በልመንህ ታደሰ ቀይረው ገብተዋል ።ጨዋታው ከጅምሩ በሁለቱም በኩል ፈጠን ያለ እንቅስቃሴ በማስመልከት የጀመረ ሲሆን በዚህ ሂደት ብዙም አልዘለቀም ነበር ።

አርባምንጭ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩ የተሻለ በመሆን እና የአዲስ አበባ ከተማን ተጫዋቾች የኳስ ምስረታ ሂድት በማቋረጥ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ሞክረዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ በኩል ደግሞ በሁለቱ የመስመር ተጫዋቾች እንዳለ ከበደ እና ፍፁም አለሙ አማካኝነት ወደ ሳጥኑ ለመግባት እና የፊት አጥቂውን ሪችሞንድ አዶንጎን ለማግኘት ሲያደርጎቸው የነበሩ ጥረቶች እምብዛም ተፅዕኖ የፈጠሩ አልነበሩም ።

በ16ኛው ደቂቃ ላይ አህመድ ሁሴን ከእጅ ውርወራ የተነሳ ኳስን ከተከላካዮች አምልጦ ማግኘት ችሎ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅለት ቀርቷል ። በ23ኛው ደቂቃ ላይ አዞዎቹን በዝውውር መስኮቱ የተቀላቀለው አህመድ ሁሴን ወደ ግብ የሞከረው ጠንካራ ኳስ በግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ ሲመለስ በቅርብ የነበረው በላይ ገዛኸኝ አግኝቶት አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ ዳንኤል በድንቅ ሁኔታ ዳግም መልሶ የማዕዘን ምት አድርጎታል ።ነገር ግን አርባምንጭ ከተማዎች በኳሱ መሳት ተገርመው እጃቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ ሳያወርዱ ግብ አግኝተዋል ። የማዕዘን ምቱን ሙና በቀለ ሲያሻማው ፀጋዬ አበራ ከመረብ ላይ አሳርፎታል ።
ከግቡ በኋላ አዲስ አበባ ከተማዎች የተሻለ ለመንቀሳቀስ የጣሩ ቢሆንም ሙሉቀን አዲሱ እና እንዳለ ከበደ ከሳጥን ውጪ ሞክረው ኢላማቸውን ከሳቱባቸው ኳሶች ውጪ የግብ ሙከራ ሳያደርጉ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል ።ሁለተኛውን አጋማሽ በቅያሪዎች የጀመሩት አዲስ አበባ ከተማዎች የማጥቃት አቅማቸውን አጠናክረው መቅረብ የቻሉ ሲሆን በዚህም 56ኛው ደቂቃ ላይ አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ አግኝተዋል ።
ኳሱ በሳሙኤል አስፈሪ አማካኝነት ከማዕዘን ሲሻገር ጋናዊው አጥቂ ሪችሞንድ አዶንጎ በግንባር በመግጨት በሳምሶን አሰፋ መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል ።

ከግቡ በኋላ አዲስ አበባ ከተማዎች ሁለተኛ ግብ ለማከል ብልጫውን ወስደው መቀጠልም ችለው ነበር ። በዚህም ፍፁም ጥላሁን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ግብ አስቆጣሪው አዶንጎ ወደ ግብ ቢልከውም በግብ ጠባቂው ተይዞበታል ።

በአጋማሹ ብልጫ ከመወሰድም ባለፈ ግብ ያስተናነዱት አዞዎቹ በ65ኛው ደቂቃ ላይ ዳግም መሪ መሆን ችለዋል ። የመጀመሪያውን ግብ በጥምረት ያስቆጠሩት አቀባዩ ሙና በቀለ እኔ ፀጋዬ አበራ ዳግም በተጣመሩበት አጋጣሚ ፀጋዬ በግንባር በመግጨት በዳንኤል ተሾመ መረብ ላይ አሳርፏል ።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች የመዲናዋ ክለብ ተጫዋቾች መልሰው አቻ ለመሆን ጥረቶች ማድረጋቸውን ቢቀጥሉም ግብ ማስቆጠር ቀላል አልሆነላቸውም ። በ77ኛ ደቂቃ ላይ ሪችሞንድ አዶንጎ ፊት ለፊት ከሳምሶን አሰፋ ጋር ተገናኝቶ አስቆጠረው ተብሎ ቢጠበቅሞ ኳሱን መጠቀም ሳይችል ቀርቷል ።

በመጨረሻም አርባምንጭ ከተማ በፀጋይ አበራ ሁለት ግቦች አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል ።ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ነጥቡን 22 በማድረስ ወደ 8ኛ ደረጃ ከፍ ሲል አዲስ አበባ ከተማ በበኩሉ በ15 ነጥብ በ14ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሰኞ ቀን 9 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን ሲገጥም አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት መከላከያን ይገጥማል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...