መነሻ ገጽ መከላከያ የጨዋታ ዘገባ | የመከላከያ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል
መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የመከላከያ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

በ16ኛው ሳምንት ውሎ በቀዳሚነት የተደረገው የመከላከያ እና የአርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።

መከላከያዎች በ15ኛው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ አራት ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን አዳዲስ ፈራሚዎቹን አሚን ነስሩ ፣ ምንተስኖት አዳነ እና እስራኤል እሸቱን ጨምሮ ቢንያም በላይን በቋሚ አሰላለፍ ያካተቱ ሲሆን በአርባ ምንጭ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከሰበታ ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ በነበረው ምርጥ 11 ያልተካተቱትን ስድስት ያህል ማለትም በርናንድ ኦቼንጌ ፣ አንዱአለም አስናቀ ፣ መሪሁን መስቀለ ፣ ሙና በቀለ ፣ ሀቢብ ከማል እና ከወልቂጤ ከተማ ያስፈረሙትን አህመድ ሁሴንን በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል ።ጨዋታው በሙሉ ዘጠና ደቂቃ ያን ያህል ሳቢ ያልነበረ እና ምንም አይነት ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ያላስመለከተን ነበር ።

አዳዲስ ፈራሚዎቻቸን በማሰለፍ ጨዋታውን መጀመር የቻሉት በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚመሩት መከላከያዎች በመጀመሪያ አጋማሽ በተለይም እስከ ዉሀ እረፍት ድረስ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ ወደ ግብ ክልል መቅረብ ችለው ነበር ።

በተወሰነ ከመስመር በሚነሱ እና ከቆሙ ኳሶች የአርባምንጭን የተከላካይ መስመር ለመፈተን ያደረጓቸው ጥረቶች እምብዛም ተጋጣሚያቸውን መፈተን ያልቻለሉ ሲሆን በ9ኛው ደቂቃ ላይ ላርዬ ኢማኑኤል ከሳጥን ውጪ አክርሮ ሞክሮ ወደ ውጪ ከወጣበት ኳስ ውጪ ሌላ የግብ ዕድል መፍጠር አልቻሉም ነበር ።

በአዞዎቹ በኩል ከውሀ እረፍት መልስ በአመዛኙ ጥሩ ለመንቀሳቀስ የሞከሩ ቢሆንም ልክ እንደ መከላከያ የተጋጣሚያቸውን ግብ ጠባቂ መፈተን ሳይችሉ አጋማሹን አጠናቀዋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተለየ እንቅስቃሴ ያልታየበት ነበር ።
መከላከያዎቹ በአንፃራዊነት ኳሱን ይዘው በመጫወት እና በተለይም በሁለቱ መስመሮች በኩል ወደ አርባ ምንጭ ከተማ ሳጥን ለመግባት ፍላጎት ያሳዩ ቢሆንም ያንን ለማድረግ በዕጅጉ ተቸግረው ነበር ።

በአርባ ምንጭ ከተማ በኩልም በተለይም የአጋማሹ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ አህመድ ሁሴን ኢላማ ያደረጉ ኳሶች ወደ ፊት ለማድርስ ሙከራዎችን ቢያደርጉም የጦሩን የተከላካይ መስመር ማለፍ የቻሉ ግን አልነበሩም ።

በ75ኛው ደቂቃ ላይ ወርቅይታደስ አበበ ከቀኝ መስመር ወደ ግብ ክልል የላከውን ኳስ ተቀይሮ የገባው ፍቃዱ ሳይደርስበት ቀረ እንጂ ለአዞዎቹ ጥሩ የግብ አጋጣሚ መሆን የሚችል ኳስ ነበር ። በመከላከያ በኩል በተደጋጋሚም ከቆሙ ኳሶች የሚሻገሩ ኳሶች የታሰበቀት ቦታ ላይ ሳይደርሱ ሲበላሹ የቆዩ ሲሆን በ80ኛው ደቂቃ ላይ ግን ቢንያም በላይ ያሻማውን የማዕዘን ምት ግሩም ሀጎስ ነፃ ሆኖ አግኝቶ በግንባር ወደ ግብ ቢልከውም ኳሱ ኢላማውን መጠበቅ ሳይችል ወደ ውጪ ወጥቷል ።
ጨዋታውም ምንም ግብ ሳይስተናገድበት ፍፃሜውን አግኝቷል ።ከጨዋታው በፊት በእኩል 18 ነጥብ ላይ የነበሩት ሁለቱ ክለቦች ነጥባቸውን በአንድ ከፍ ማድረግ ሲችሉ በደረጃቸው ላይ ግን ለውጥ ሳያመጡ በ10 ( አርባምንጭ ከተማ ) እና 11ኛ ( መከላከያ )ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገደዋል ።

በ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መከላከያ በመጪው ማክሰኞ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሰበታ ከተማን ሲገጥም አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ሀሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...