መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | የአዳማ ከተማ እና የሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል
ሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የአዳማ ከተማ እና የሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ አዳማ ከተማን ከሀድያ ሆሳዕና አገናኝቶ ቀዝቃዛ ጨዋታን አሳይቶ በሁለቱም በኩል ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ሊጠናቀቅ ችሏል ።

በሀድያ ሆሳዕና በኩል ከሶስተኛ ሳምንት ጨዋታቸው አራት ቅያሪዎችን ያደረጉ ሲሆን አበባየሁ ዮሀንስን መላኩ ወልዴን ቃልአብ ውብሸትን እና እያሱ ታምሩን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ማካተት ችለዋል ። በአዳማ ከተማ በኩል ደግሞ ካለፈው ጨዋታ ቋሚ 11 ሶስት ቅያሪዎችን ያደረጉ ሲሆን ጀማል ጣሰው ጀሚል ያዕቆብ አብዲሳ ጀማል በሶስተኛው ሳምንት በወላይታ ድቻ በተሸነፉበት ጨዋታ በቋሚ አሰላለፍ ያልነበሩና በዛሬው ጨዋታ በቋሚነት የመሰለፍን ዕድል ማግኘት የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው ።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በሁለቱም በኩል ወደ ግብ ክልል በመድረስ ረገድ ክፍተቶች የነበሩበት ነበር ። 15ኛው ደቂቃ ላይ ዑመድ ዑክሪ ወደ ግብ የሞከረው እና በጀማል ጣሰው የተመለሰው ኳስ በመጀመሪያው አጋማሽ የታየ ብቸኛ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ነበር ።

በ43ኛው ደቂቃ ላይ አንድ አወዛጋቢ ክስተት ተፈጠረ ። ከራሱ ተጫዋች ኳስ የተላከለት የሀድያ ሆሳዕናው ግብ ጠባቂ ሶሆሆ ሜንሱ ኳሱ በማጠሩ ምክንያት ወቶ ሊደርስበት ሲሞክር ዳዋ ሆቴሳ ቀድሞ ደርሶበት ለማለፍ ሲሞክር ከሳጥን ውጪ በእጁ ነክቶት ሊመልሰው የቻለ ሲሆን በዚህም የዕለቱ የመሀል ዳኛ የቢጫ ካርድ ያሳዩት ሲሆን በውሳኔው ያልተደሰቱት የአዳማ ከተማ ተጨዋቾች በዳኛው ውሳኔ ተቃውሞአቸውን ያሳዩ ሲሆን ክለቡም ወድያውኑ ክስ አስይዟል ።

በሁለተኛው አጋማሽም በተመሳሳይ እንደመጀመሪያው አጋማሽ የግብ ሙከራዎች ያልታጀበ ሲሆን 57ኛ ደቂቃ ላይ ዳዋ ሆቴሳ ከቅጣት ምት የመታው ኳስ በግብ ዘቡ ሶሆሆ ሜንሱ ተመልሷል ። በአጋማሹ አዳማ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥር በተሻለ መንገድ በመንቀሳቀስ የተጫወቱ ቢሆንም ግብ ለማስቆጠር ግን ተቸግረዋል በተመሳሳይ በሀድያ ሆሳዕና በኩልም ወደ ግብ ክልል በመድረስ የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ ያደረጉት ጥረት የተሳካ አልነበረም ።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ አምስት ያህል ደቂቃዎች ሲቀሩት የሀድያ ሆሳዕናው መላኩ ወልዴ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ። በመጨረሻም ጨዋታው ምንም ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቀቀ ።

በዚህም መሰረት ሀድያ ሆሳዕና ሁለተኛ ነጥባቸውን ሲያገኙ አዳማ ከተማዎች ከነበራቸው አራት ነጥብ ላይ አንድ ነጥብ በመጨመር አምስተኛ ነጥባቸውን አስመዝግበው ወተዋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...