በተጠናቀቀው የዉድድር አመት ከመዉረድ ለጥቂት የተረፉት ሲዳማ ቡናዎች ለቀጣዩ የ2014 አመት ተፎካካሪ ሆነዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በክረምቱ የዙዉዉር መስኮት ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዉ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ መጀመራቸዉ ይታወሳል።
በትላንትናው ዕለት ግብ ጠባቂዉን መክብብ ደገፉ የግላቸዉ ማድረግ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ለሩዋንዳዊዩ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ካዩምባ ሶተር የሙከራ ዕድል መስጠታቸው ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ክለቦች ለኤስ ኪጋሊ እና ራዮን ስፖርት እንዲሁም ለኬንያዎቹ ሶፋፓካ ኤፍሲ እና ኤፍሲ ሊዮፖርድስ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ የ28 አመቱ ካዩምባ በዛሬዉ ዕለት ክለቡን ተቀላቅሎ ልምምዱን የከወነ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በሚኖሩት የልምምድ መርሀግብሮች ላይ ጥሩ የሚንቀሳቀስ ከሆነ እና አሰልኛኙን ማሳመን ከቻለ በቋሚነት ፊርማዉን እንደሚያኖር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
አስተያየት ይስጡ