ለቀጣዩ የ2014 የዉድድር አመት በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲያስፈርሙ የቆዩት ድሬዳዋ ከተማዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የፊት መስመር አጥቂያቸዉን ሙኸዲን ሙሳ ዉል ለተጨማሪ አንድ አመት ማራዘማቸው ተረጋግጧል።
ከናሽናል ሲሚንት በ2010 ዓ.ም ድሬዳዋ ከተማን የተቀላቀለዉ አጥቂዉ በመሀል ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቶ 2011ን በከፍተኛ ሊጉ ማሳለፉ አይዘነጋም። በዚያዉ የዉድድር አመት ወደ ቀድሞ ክለቡ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ በመመለስ እስከተገባደደዉ የ2013 አመት ድረስ ክለቡን በማገልገል ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ምንም እንኳን ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት ቢኖረዉም በስምምነት ለተጨማሪ አመት ከብርቱካናማዎቹ ጋር ለመቆየት ፊርማዉን አኑሯል።
አስተያየት ይስጡ