በዘንድሮው የዉድድር አመት በሀድያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ ዉስጥ ድንቅ የሚባል አመትን ያሳለፈዉ ተከላካዩ ሔኖክ አርፌጮ ከክለቡ ጋር ያለዉ ቆይታ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።
በዉድድር ዓመቱ ጥሩ ብቃት ማሳየት ከቻሉት እና ነጥረዉ ከወጡት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነዉ አማካዩ ሄኖክ አርፊጮ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር በዝዉዉር ጉዳይ ስለመያያዙ እና ተያያዥ ጉዳዮች ተከታዩን ሀሳብ ለሀትሪክ ስፖርት ሰጥቷል ።
ሀትሪክ:- ከክለቡ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ስላለው ቆይታ?
ሄኖክ:- እንደሚታወቀዉ ዘንድሮ በሊጉ ጥሩ የሚባል የዉድድር አመትን ማሳለፍ ችለናል በሀድያ ቤትም ረጅም አመት እንደመቆየቴ ለክለቡ የተለየ ፍቅር እና ክብር አለኝ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ክለቡ ከእኔ ጋር ምንም አይነት ንግግር አላደረግንም።
ሀትሪክ:- ሌሎች ክለቦች ከአንተ ጋር ንግግር ጀምረዋል ስለመባሉ?
ሄንክ:- እዉነት ነዉ! አንድ አንድ ክለቦች አናግረዉኛል እያናገሩኝም ነዉ። በተለይ ስማቸዉን መጥቀስ የማልፈልጋቸዉ አንድ ሁለት ክለቦች የሊጉ የመጨረሻ መርሀግብር ሀዋሳ ላይ ሲደረግ ጀምሮ በደንብ ገፍተዉ በምጣት እያናገሩኝ ነዉ። ነገር ግን እንደነገርኩህ ለክለቤ ሀድያ የተለየ ክብር ስላለኝ እስካሁን ምንም ያደረኩት ስምምነት የለም። ከክለቤ ሀድያ ሆሳዕና የሚመጣውን ነገር እየጠበኩ ነዉ!!
ሀትሪክ:- ከክለብህ ሀድያ ሆሳዕና ጋር እስከ አሁን ስለቆይታህ ያልተነጋገርክበት ምክንያት ምን ይሆን?
ሄኖክ:- ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ አላዉቅም። ነገር ግን እኔ አሁንም ከየትኛውም ክለብ ጋር ያደረኩት ስምምነት የለም ክለቤ ሀድያ ሆሳዕና አንድ አንድ ፋሲሊቲዎችን አሟልቶ እንቅስቃሴ ሲጀምር ያናግሩኛል ብየ አስባለሁ።

ሀትሪክ :- በቀጣይ የሄኖክ አርፌጮ ዉሳኔ ምን ሊሆን ይችላል?
ሄኖክ:- ያዉ የተሻለ ነገር ማንም አይጠላም ነገር ግን ለክለቡ ረጅም አመት እንደመጫወቴ የምሰጠዉ ክብር አለ ከሌሎች ክለቦች ደግሞ የሚመጡትን ጥያቄዎች በሚገባ አይቼ በተለይ በደንብ ገፍቶ የመጣ አንድ ክለብ አለ ያ ክለብ የሚያቀርብልኝን ነገር ተመልክቼ ለኔ የተሻለ ነገር ነዉ ይጠቅመኛል ብየ የማስበዉን ነገር የምወስን ይሆናል።
በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሊጉ አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ የቻለዉ ሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾቹን በሚገባ መንገድ በመያዝ ለቀጣዩ የዉድድር አመት ከማዘጋጀት ይልቅ ከዚህ በተቃራኒው ተጫዋቾቹ ጋር በክስ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
አስተያየት ይስጡ