መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ጅማ አባጅፋር ወልዲያ ከተማን በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል 
ሪፖርትወልዲያየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ሪፖርት | ጅማ አባጅፋር ወልዲያ ከተማን በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል 

አጋራ
አጋራ

በዮናስ ምስጋናው

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ወልድያ ከተማን ያስተናገደው ጅማ አባጅፋር በኦኮኪ አፎላቢ 64ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ማሸነፍ ችሏል፡፡

በጨዋታው እንቅስቃሴ 10 ያህል ልጆችን በግል ና በጉዳት ምክንያት ያላካተተው ወልድያ አጠቃላይ ለጨዋታው 14 ልጆችን ብቻ ማስመዝገቡ እና ባሳለፍነው ረቡዕ ከመቀሌ ጋር ጨዋታ አድርጎ ከ3 ቀናት በሃላ መጫወቱ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ደካማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ተመሳሳይ የ 4-4-2 አጨዋወት ይዘው የገቡት ሁለቱም ብድኖች አዝናኝ እግርኳስ ከመጫወት ይልቅ በመልሶ ማጥቃት ና የክንፍ ኳሶችን ለመጠቀም ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡


በእለቱ ጨዋታውን ሲመሩ የነበሩት ዋና ዳኛ ኢብራሂም አጋዥ 5 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመዙ 3ቱን ለጅማአባጅፋር እንዲሁም 2ቱን ለወልድያ ሰተዋል፡፡
በእለቱ ለጅማአባጅፋር የወልዲያ ተጫዋቾች ኳስ፡እዳይቆጣጠሩ እና ከአጥቂወች ጋር እዳይገናኙ በማድረግ ሲከላከሉ ቆይተዋል፡፡የጨዋታ ልዩነት የነበረው ከጅማ በኩል አማን ነስሩ የወልዲያ ከተማ የመሐል ክፍልን ኳሶችን በማጨናገፍ እና በመቁረጥ ትልቁ ድርሻ የነበረው ሲሆን  ግዙፉን አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በሚገባ የተቆጣጠረው የወልዲያው  ዳንኤል ደምሱ የጨዋታው ኮከብ ነበሩ፡፡

ጅማ አባጅፍር ውጤቱን ተከትሎ 3ደረጃ ሲይዝ ወልድያ 12 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ -ጅማ አባጅፋር 

“ዛሬ ቡድናችን ተጭኖ በመጫወቱ አሸንፈን ወጥተናል፡፡ በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች በዚሁ የአሸናፊነት መንፈስ እንጫወታለን፡፡”

ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ -ወልዲያ ከተማ

” እንዳያችሁት ምንም ተጫዋች የለኝም 10 ያክል ተጫዋቾቼ  በጉዳትና በተለያየ  ምክኒያት አልነበሩም፡፡ በተቀያሪ ቦታ ላይ የነበሩት ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው የነበሩን” በተከታታይ 10 ቀናት 4ጨዋታዎችን እንድናደርግ መገደዳችን ተፅእኖ ፈጥሮብናል፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...